የሸገር ኤፍ ኤም ጋዜጠኞች ከእስር ተለቅቀዋል

Date:

የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛው ችሎት የሸገር ኤፍ ኤም ጋዜጠኞች ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ፀጋው በዋስ እንዲለቀቁ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፅንቷል።

ጋዜጠኞቹ በዋስ እንዲለቀቁ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ ትላንት ከሰዓት በ21ኛ ቀናቸው ከእስር ተለቅቀዋል።

የፌዴራሉ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ፣ጋዜጠኞቹን ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ፀጋው በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ፣ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት፣ ለፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ነበር፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው የጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ነገሩን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ትላንት መስከረም 14 ቀን 2018 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡

ጋዜጠኞችቹ ትዕግስት ዘሪሁንና ምንታምር ፀጋው በቁጥጥር ስር በዋሉ 21ኛው ቀን በተለዋጩ ቀጠሮ ቀን ፣ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የስር ፍርድ ቤት በዋስ እንዲለቀቁ የሰጠው ውሳኔ አፅድቆ መዝገቡን ዘግቷል፡፡

በውሳኔው መሰረት ትላንት ከሰዓት ከእስር ተለቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...