የሉፍታንዛ አየር መንገድ  በ2030  የአስተዳደር ስራዎችን በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ሊቀይር ነው

Date:

ሉፍታንዛ በ2030 4000 የሚሆኑ የአስተዳደር ስራዎችን በዲጂታላይዜሽን እና በኦቶሜሽን ለመቀነስ ማቀዱን አስታውቋል።

አየር መንገዱ አንዳንድ ስራዎች ከነጭራሹ ከዚህ በኋላ አያስፈልጉም ያለ ሲሆን ስራውን የተቀላጠፈ ለማድረግ እንደ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ያሉ እና ሌሎችም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እንደሚጠቀም ገልጿል።

ስራን ከማቀላጠፍ በተጨማሪ አየር መንገዱን በዚህ መንገድ ማዋቀር ትርፋማ ያደርገዋል ተብሏል።

የተለያዩ አየር መንገዶች ከኪሳራ ጋር በተያያዘ ሰራተኛ ሲቀንሱ ስፕሪት የተሰኘው አየር መንገድ በዚህ አመት ለሁለተኛ ጊዜ ኪሳራ ማስተናገዱን ተከትሎ 1800 የበረራ ሰራተኞችን ሲያሰናብት ባለፈው ሐምሌ 270 አብራሪዎችን ማባረሩ ይታወሳል።

እንደ ስዊዝ እና ብራሰልስ አየር መንገድ ያሉትን በውስጡ የያዘው የሉፍታንዛ አየር መንገድ ፊቱን ወደ ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ማዞሩ መጪው ጊዜ ምን ሊሆን እንደሚችል ያሳየ ሆኗል።

በ2030 በአለም አቀፍ ደረጃ ከ92 ሚሊየን በላይ ስራዎች በሰው ሰራሽ አስተውህሎት የተነሳ እንደሚቀነሱ ወይም እንደሚተኩ የአለም ኢኮኖሚ ፎረም መተንበዩ ይታወሳል።

የመረጃው ምንጭ Fox News ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...