ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር የሆነው የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ፤ የትኩረት አቅጫውን በሚጠቁም መልኩ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ “የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ“ በሚል ስያሜ የሚጠራ መሆኑን ገልጿል፡፡
የስያሜ ለውጡ ተቋሙ በፐብሊክ ሰርቪስ ትምህርት፣ ምርምር እና አመራር የልህቀት ማዕከል ለመሆን የያዘውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
በዚህም የዩኒቨርሲቲው ይፋዊ ድረ-ገፅ እና የማኅበራዊ ትስስር ገፆች በአዲሱ ስያሜ የሚቀየሩ ሲሆን፤ የተቋሙ ሰራተኞች እንዲሁም የቀድሞ እና የአሁን ተማሪዎች አዲሱን ስያሜ እንዲጠቀሙ ተጠይቋል፡፡
የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ እና ከፐብሊክ ሴክተር ተቋማት የተመለመሉ ተማሪዎችን በቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች መቀበሉ ይታወቃል ።
