የአማዞን ዋና ስራ አስፈፃሚ አንዲ ጄሲ በአሁኑ ወቅት አማዞን ከ1000 በላይ የጄኔሬቲቭ ኤአይ አገልግሎቶች እና መተግበሪያዎች እንዳሉት ገልፀው ይህም ከሚያስቡት አንፃር በጣም ጥቂት እንደሆነ አንስተዋል።
አማዞን ከሰው ሰራሽ አስተውህሎቱ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የስራ ቅነሳ ያደርጋል ሲባል ተቋሙ በዛው ልክ ቴክኖሎጂው ላይ ከፍተኛ ገንዘብ የማውጣት እቅድን ይዟል።
በኖርዝ ካሮላይናም የሰው ሰራሽ አስተውህሎት መሰረተ ልማቱን ለማጠናከር 10 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስት እንደሚያደርግ ገልጿል።
አማዞን የስራ ቅነሳው ቢሮክራሲን እንደሚቀንስ እንደዚሁም ሃብትን አሁን ያለውን እና የሚመጣውን ደንበኛ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በተገቢው ቦታ ኢንቨስት ለማድረግ ይረዳል ብሏል።
በስራ ቅነሳው የሚካተቱ ሰዎች በዛው በአማዞን አዲስ የስራ ዘርፍ እንዲፈልጉ 90 ቀናት እንደሚሰጣቸው ተገልፆ ያላገኙት ግን ጥቅማ ጥቅምና ካሳ ተሰጥቷቸው እንደሚሰናበቱ አማዞን ገልጿል።
አማዞን አጠቃላይ 350,000 የኮርፖሬት ሰራተኞች ያሉት ሲሆን የዛሬው ቅነሳ 4 በመቶውን ያህል ሰራተኛ ያካተተ ነው።
ከሰው ሰራሽ አስተውህሎት ማደግ ጋር በተያያዘ በርካታ ድርጅቶች ተመሳሳይ እርምጃ እየወሰዱ ይገኛሉ።
tikvahethmagazine
