በኢትዮጵያ 83 በመቶ የሚሆነው የማህበረሰብ ክፍል ምግቡን የሚያበስለዉ በባህላዊ መንገድ ነው

Date:

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሃይል አማካሪ አቶ ጎሳዬ መንግስቱ፤ በኢትዮጵያ 83 በመቶ የሚሆኑት ዜጎች ምግባቸውን የሚያበስሉት በባህላዊ መንገድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

10 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ጭስ አልባ ምድጃዎችን የሚጠቀሙት ያሉት አቶ ጎሳዬ፤ይህ ማለት ከአምስት ሴቶች አራቱ በከሰል፣በኩበትና ሌሎች ባህላዊ መንገዶችን ነው የሚጠቀሙት ብለዋል።

አቶ ጎሳዬ ይህም በርካቶችን ለከፍተኛ ጉዳትና ሞት ፤ ለአየር ንብረት ብክለት እየዳረገ ይገኛል ሲሉ አስረድተዋል።

ለዚህም ምክንያቱ የግንዛቤ እጥረት፣የማብሰያዎቹ ዋጋ መናር እንዲሁም የግብዓቶቹ በየስፍራው በተገቢው መንገድ ተደራሽ ያለመሆን በዋናነት ይጠቀሳሉ ነው ያሉት።

አማካሪው ይህን ያሉት በግሪን ሲ ኢነርጂ ተገጣጥሞ ለገበያ የቀረበውን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና ታዳሽ የምግብ መስሪያ የ”ኢንዳክሽን ምድጃዎችን” ባስመረቁበት ወቅት ነው።

ሆኖም ዘመናዊ ጭስ አልባ ምድጃዎችን መጠቀም የህፃናትና እናቶችን ጤና ከማስጠበቅ ባለፈ የደን መጨፍጨፍን በመዋጋት ፣የቤትን ውስጥ ደህንነትን በማጎልበት እና የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ ይደግፋል ሲሉ አስረድተዋል።

የስማርት ከተማ ልማት ፕሮግራሞችን ይደግፋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የግሪን ሲን መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ረቂቅ በቀለ ፤ይህ ቴክኖሎጂ በዓመት 63 ሺህ ለሚገመቱ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን የቤት ውስጥ የአየር ብክለትን በመቀነስ ይታደጋል ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ ወ /ሮ ረቂቅ፤ሴቶች ማገዶን በመሰብሰብ እንዲሁም ምግብ ለማብሰል የሚያባክኑትን ከ5መቶ በላይ ሰአታት በመቆጠብ ረገድ ይህ ዘመናዊ የምግብ ማብሰያ ምድጃ ጉልህ ጠቀሜታ አለው ሲሉ ገልፀዋል።

ምድጃው አነስተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ይጠቀማል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፤ በሶላር ሃይልም አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል።

ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...