ወደ ነጩ ቤተመንግሥት ሲገቡ ይዘውት ከመጧቸው ሃሳቦች መካከል አንዱ በሃገራት ላይ ታሪፍ መጣል የነበረው ትራምፕ አሁን ደግሞ ከታሪፉ ገቢ ለአሜሪካውያን የድርሻ ክፍፍል አደርጋለሁ ብለዋል።
ትራምፕ ከፍተኛ ገቢ ከሚያገኙ አሜሪካውያን በስተቀር ሁሉም ዜጋ 2000 ዶላር እንደሚሰጠው ተናግረዋል።
ትራምፕ” ከታሪፍ በተቃራኒ የሚቆሙ ሰዎች ሞኝ ናቸው፤ አሁን ላይ በጣም ሃብታም እና የምንከበር የአለማችን ሃገር ነን። የኑሮ ውድነት የለም፤ የአክሲዮን ገበያው ሪከርድ ላይ ነው” በማለት “ለሁሉም ከከፍተኛ ገቢ ከሚያገኙት ውጪ 2000 ዶላር ይከፈላል” ብለዋል።
የገንዘብ ሚኒስትሩ ስኮት ቤሰንት ስለ ክፍያው ከትራምፕ ጋር አልተነጋገርኩም ያሉ ሲሆን ክፍያው በቀጥታ ከመስጠት ውጪ ታክስ እና ብድር እንደመቀነስ ባሉ አማራጮች ሊሰጥ ግን ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።
ትራምፕ ሁሉም ሃገር ላይ ማለት በሚቻል ደረጃ ታሪፍ የጣሉ ሲሆን ይኸው ታሪፍም ከፍተኛ ገቢ በማምጣት አሜሪካን ባለጸጋዋ ሃገር እንዳደረጋት ተናግረዋል።
ዘገባው የኤቢሲ ነው።
@TikvahethMagazine
