ያለጊዜያቸው የተወለዱ ጨቅላ ሕጻናትን ቀን በማስመልከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ተካሄደ

Date:

25ኛ አመቱን ለማክበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው፤ ፍቅረ ሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል  ያለ ጊዜያቸው የተወለዱ ጨቅላ ሕጻናትን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር አካሄዷል፡፡

ፍቅርሰላም ሆስፒታል 25 ዓመቱን ሲያከብር ከሚያከናውናቸው 25 በጎ ነገሮች አንዱ፤ በህዳር 20 – 2018 ዓ.ም መርሀ ግብር እንደሆነ ተነግሯል።

ሆስፒታሉ ባለፈው ሐሙስ የደም ልገሳ አሰባስቦ የነበረ ሲሆን፤ የሆስፒታሉ መሥራች ዶክተር ፍቅረማሪያም ጉደታ ማህበራዊ ኃላፊነት መወጣት ትልቁ ሥራችን ነው ብለዋል።

በመርሃ ገብር የተገኙት የጨቅላ ሕጻናት ሠብ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ሙሉዓለም ገሠሠ በበኩላቸው፤ ያለጊዜ መወለድ በልዩ ልዩ ምክንያቶች የሚያጋጥም መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም፤ በጉዳዩ ላይ የባለሙያ ምክርና ግንዛቤ ለወላጆች እና ለህብረተሰቡ ማስያዝ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሆስፒታሉ ከሕክምና አገልግሎት ጎን ለጎን የተለያዩ በጎ አድራጎት ሥራዎችን እየሰራ እንደሚገኝና ይህን ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ከተመሠረት 25 ዓመቱን ያስቆጠረ ሲሆን፤ በ3 ሰራተኛ የጀመረው ሆስፒታሉ አሁን ላይ 250 ለሚደርሱ ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩ ተገልጿል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...