ኤምባሲው ይህንን የገለጸው በዘርፉ ቀዳሚ ከሆኑ የአሜሪካ አቪየሽን ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው “አፍሪክኤር” ኩባንያ ከኢትዮጵያ መንግስት እና የግሉ ዘርፍ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ከሰሞኑ በአዲስ አበባ የተካሄደ ሁነትን አስመልክቶ ባስተላለፈው መልእክት ነው።
የአሜሪካው የግል አቪየሽን ኩባንያ አፍሪክኤር ከሕዳር 1 እስከ ሕዳር 9 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ባካሄደው መርሃ ግብር “ሴስና ስካይ ኮሪየር” የተባለ አዲስ የአውሮፕላን ምርት ለዕይታ ያቀረበ ሲሆን የመጀመሪያ የሙከራ በረራውንም ወደ ደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ አድርጓል።
በጉዞው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጭምር መሳተፋቸውን የገለጸው የአሜሪካ ኤምባሲ፤ በአዲስ አበባ በተካሄደው መርሃ ግብር “አፍሪክኤር” ከሎጅስቲክስ እስከ ሰብዓዊ እርዳታ ድረስ፤ በሁሉም ኢንዱስትሪዎች የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ረገድ የግል የአቪየሽን ዘርፉ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግስት እና የግሉ ዘርፍ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት መደረጉን ገልጿል።
የአሜሪካና ኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ትስስር በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ አቪየሽን ዘርፍ እየተጫወተ ስለሚገኘው ቁልፍ ድርሻም ኤምባሲው ጠቅሷል።
በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አቪየሽን ኢንዱስትሪ በአሜሪካ ከ100 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ሥራዎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑንና በዚህም ዘርፉ ለሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት መጠናከርና የጋራ ብልጽግና ቁልፍ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ መሆኑን ኤምባሲው ጠቅሷዓል።
“በዘርፉ ተባብሮ ለመስራትና በጋራ ለማደግ በአሁኑ ሰዓት አፍሪኬር በኢትዮጵያ አቪየሽን ውስጥ እያደረገ የሚገኘው ጥረትም ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው” ያለው ኤምባሲው፤ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ኩባንያውን በመደገፉ ኩራት የሚሰማው መሆኑን ገልጿል።
አዲስ ማለዳ
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
Twitter ➲ t.ly/mxA
