Date:

የመከላከያ አቅሞችን የምናጎለብተው “ለመዋጋት አይደለም” – ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ 

ኢትዮጵያ የመከላከያ አቅሟን የምታጎለብተው “ትናንሽ አቅም ይዘው ለሚሳሳቱ ኃይሎች ብዙ ጊዜ [ሰጥተው] እንዲያስቡ ለማስቻል” እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እነዚህን አቅሞች የምናጎለብተው ለመዋጋት አይደለም። ውጊያን ለማስቀረት ነው” ብለዋል።

አብይ ይህን ያሉት “ስካይ ዊን ኤሮኖቲክስ ኢንዱስትሪ” የተባለ የሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖች) ማምረቻ ትላንት ቅዳሜ የካቲት 29፤ 2017 በመረቁበት ወቅት በሰጡት ገለጻ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውሉ ምርቶችን በሚያመርቱ ፋብሪካዎች ተገኝተው ማብራሪያ ሲሰጡ፤ የትላንቱ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።

ባለፈው ረቡዕ በኦሮሚያ ክልል አምቦ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘውን የሆሚቾ ጥይት ፋብሪካ የጎበኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ ኢትዮጵያ ከወታደራዊ ግብዓት አንጻር የነበረባትን “ውስንነት ከሞላ ጎደል ፈትታለች” ብለው ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፋብሪካ ጉብኝትም ሆነ ያቀረቡት ገለጻ፤ ኢትዮጵያ “ከኤርትራ ጋር ወደ ሌላ ዙር ጦርነት ለመግባት በዝግጅት ላይ ለመሆኗ ማሳያ” አድርገው የቆጠሩ ወገኖች አሉ።

ይህን አመለካከት የተረዱ የሚመስሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በትላንቱ ገለጻቸው፤ “እነዚህን አቅሞች የምናጎለብተው ለመዋጋት አይደለም። ውጊያን ለማስቀረት ነው። ትናንሽ አቅም ይዘው ለሚሳሳቱ ኃይሎች፤ ብዙ ጊዜ [ሰጥተው] እንዲያስቡ ለማስቻል ነው። ውጊያን ለማስቀረት (deter) ለማድረግ ከፍተኛ አቅም ስላለው ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

ቀዳሚ ጽሑፍ
ቀጣይ ጥሑፍ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...