ኢዜማ አራት ጉዳዮችን የያዙ አጀንዳዎች ለኮሚሽኑ ማስረከቡን አስታወቀ

Date:

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ) ‘ሕገ-መንግሥት ይሻሻል’ የሚለውን ጨምሮ፤ አራት ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ አጀንዳዎቹን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ማስረከቡን አስታውቋል። 

የፓርቲው የሥራ አስፈፃሚ አባልና የምክክሩ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ እዮብ መሳፍንት እንዳስታወቁት፤ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተቋቋመ ጀምሮ እያካሄደው ባለው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ፓርቲው ሲሳተፍ ቆይቷል።

በትናንትናው ዕለት ደግሞ  ፓርቲው ያመነባቸውን እና “ሀገርን ከችግር አረንቋ ውስጥ ያወጣሉ” ብሎ ያሰባቸውን አራት ጉዳዮች በአጀንዳነት ለምክክሩ አቅርቧል ሲሉ ተናግረዋል።

ፓርቲው ከአቀረባቸው አጀንዳዎች መካከል፤ ‘የሀገር ሕልውና እና ቀጣይነትን ማስጠበቅ ይቻላል ወይ?’፣ ‘የዜጎች ሰብዓዊና ዜጋዊ ደህንነታቸው ማከበር ይቻላል ወይ?’፣ ‘ከድህነትና ከኋላ ቀርነት መላቀቅ እንዴት እንውጣ?’ እንዲሁም፤ ‘የጋራ ማንነት፣ ጥቅም ፍላጎትና ስሜት ማዳበር እንዴት ይቻላል?’ የሚሉ መሆናቸውን አቶ እዮብ ገልጸዋል።

የኢዜማ ሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ መነሻ ሰነድ ዋና ዓላማ፣ በፓርቲው በኩል በሀገራዊ ምክክር የሚቀርቡ አጀንዳዎች መሠረታዊ ሀገራዊ ችግሮች ላይ ያተኮሩ፣ ከአረጃጀታቸው ጀምሮ እስከ መፍትሄ ሀሳቦቻቸው የተሻሉ እና ግልጽነት ያላቸው ሀሳቦች እንዲሆኑ በማድረግ፣ በፓርቲው አመራርና በተለያዩ ደረጃዎች የሚገኙ አካላት ውስጥ ሊኖር የሚገባውን የጋራ ግንዛቤ ለማስረጽ የሚደረገውን ጥረት ማገዝ ነው ሲሉም አክለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...