በገሊላ ደሴት ላይ ብቸኛ የቀሩት የ107 ዓመት እናት አረፉ

Date:

በዙዋይ ደንበል ሐይቅ ገሊላ ደሴት ላይ ብቸኛ ነዋሪ የነበሩት የ107 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ እናት ወ/ሮ ኩሼ ጎንደር መሞታቸው ተገለፀ።

ገሊላ ደሴት በዝዋይ (ደምበል) ሐይቅ ላይ ከሚገኙ አምስት ደሴቶች አንዷ እና አነስተኛዋ ደሴት ናት።

የባቱ ደንበል ሀይቅ 440 ስኬዌር ኪሎ ሜትር ሥፋ ያለዉ ነዉ ፡፡ እናት ኩሼ ጎንደር ገሊላ ደሴት ላይ ለ107 ዓመት ብቻቸውን ኑሮዋቸዉን እየገፉ ነዉ።

በደሴቲቱ ከቀድሞ ጀምሮ ሰዎች ይኖሩበት የነበረ ቢሆንም ኑሮን ለመምራት ምንም አመቺ ሁኔታ ባለመኖሩ፤ ከአዛዉንቷ በቀር ሁሉም ወጥተዉ እሳቸዉ ብቻቸዉን ይኖሩ ነበር ፡፡

አዛውንቷ ‹ገሊላ ደሴት ላይ ትዳር ይዤ ስድስት ልጆችን አፍርቼበታለሁ እናም ወዴትም አልሄድም ብለው ደሴቲቱን የሙጥኝ ሲሉ ልጆቻቸው ግን ደሴቲቱን ለቀዉ›መሄዳቸዉን ተናግረዉ ነበር።

በዚህች ትንሽዬ ደሴት ላይ አንድ ገዳም ይገኛል። በገዳሙ ለአገልግሎት ከሚመላለሱ ውጪ የሚኖርበት የለም።

በዚሁ ወግ ማዕረግ ባዩበት ደሴት ስርዓተ ቀብራቸዉ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ይፈጻማል ተብሏል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...