አርቲስት አንዱአለም ጎሳ በእጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ ከታሰረ ከሁለት ቀናት በኋላ ፍርድ ቤት መቅረቡን ጠበቃው ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልጿል።
ፖሊስ እስካሁን አሻራ ማንሳቱን፣ አስከሬኑን ወደ ሆስፒታል በመላክ፣ የአስከሬን ምርመራ ማድረጉን ገልጾ የሰው ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።
“አሁን ፎቶግራፎችን ከመዝገቡ ጋር ለማያያዝ፣ የሰዎች ምስክርነት ለመስጠት እና የአስከሬን ምርመራው እስኪመጣ ድረስ ለማጣራት 14 ቀናት ያስፈልገኛል ብሏል።
የአንዱአለም ጠበቃ በበኩሉ የዋስ መብት ይሰጥ ብሎ ቢጠይቅም ፍርድ ቤት የአስክሬን ምርመራ እንስኪደርስ በማለት 13 ቀናት ድምፃዊው በማረሚያ ቤት እንዲቆይ ወስኗል።
