ምክር ቤቱ ከ55 ዓመታት በኋላ የተሻሻለውን የዕፅዋት ጥበቃና ኳራንታይን አዋጅ አጸደቀ

Date:



የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ፤ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ያህል ሲሰራበት የቆየውንና ኋላ ቀር የሆነውን የእፅዋት ጥበቃና ኳራንታይን አዋጅ የሚያሻሽል አዲስ ረቂቅ አዋጅ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።


ይህ አዲስ የጸደቀው አዋጅ ቁጥር 1400/2018 ሆኖ የሚመዘገብ ሲሆን፣ ዋነኛ ዓላማውም የሥነ ሕይወት ዕፅዋት ብልሽትንና ብክነትን መከላከል እንዲሁም ዘመናዊ የተባይ መከላከልና መቆጣጠር ሥርዓትን መዘርጋት ነው።


የዕፅዋት ጥበቃና ኳራንታይን አዋጅ ከ55 ዓመታት በፊት ወደ ሥራ የገባ በመሆኑ ለወቅታዊ ቁጥጥር አመቺ ባለመሆኑ መሻሻሉ የግድ መሆኑ ተገልጿል።


በምክር ቤቱ የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በአዲሱ አዋጅ መሠረት በዕፅዋት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም አካል ከ1 እስከ 5 ዓመት በሚደርስ እስራት እንዲቀጣ ተደንግጓል።


በተጨማሪም ተቆጣጣሪ አካላት የሕግ ጥሰት ሲፈፅሙ ወይም የጉቦ ተግባር ላይ ሲሰማሩ በቀጥታ በእስራት እንዲቀጡ መደረጉ ተገልጿል።
የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ላሌ እንደገለጹት፤ አዋጁ ደረጃውን የጠበቀ የተባይ አሰሳና ቅኝት ለማድረግ እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...