የሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ አስቸኳይ ጥሪና ምስጋና

Date:

በትግራይ ክልል በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በተፈናቃይ ወገኖች ላይ እየደረሰ ያለውን የረሃብ አደጋ አስመልክቶ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ መግለጫ ሰጥተዋል።

ፕሬዚደንቱ በቅርቡ በሕፃፅ መጠለያ ጣቢያ ያለውን አስከፊ ሁኔታ የሚያሳይ ምስል ለህዝብ ይፋ ያደረጉ ወጣቶችን በማመስገን መልዕክታቸውን ጀምረዋል።

ጀነራል ታደሰ ወረደ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ኤርትራውያን ወገናቸውን ለመታደግ እያደረጉት ያለውን የርብርብ ተግባር በራሳቸውና በክልሉ መንግስት ስም አድንቀዋል።

ይህ የተቀደሰ ተግባር ተዳክሞ የቆየውን የጋራ እሴት በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል።

እንደ ፕሬዚደንቱ ገለጻ ከሆነ፣ ችግሩ በሕፃፅ መጠለያ ብቻ የተገደበ አይደለም። በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ የሚገኙ፦

  • ከ145 በላይ የመጠለያ ጣቢያዎች በመላ ክልሉ ይገኛሉ።
  • በእነዚህ ጣቢያዎች ያሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖች በአስቸኳይ የረሃብ አደጋ ላይ ናቸው።

የፌደራል መንግስት፣ የክልል መንግስታትና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተፈናቃዮችን ከሞት የመታደግ “ሰብአዊ ግዴታ” እንዳለባቸው ያሳሰቡት ጀነራል ታደሰ፤ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ የሚከተሉትን ነጥቦች አጽንኦት ሰጥተዋል፦

  • ተፈናቃዮች ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ማድረግ።
  • የፌደራል መንግስት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የመልሶ ማቋቋም ስራውን እንዲያፋጥን።

“ተፈናቃዮችን ወደ ቦታቸው መመለስና ማቋቋም ለዚህ ችግር ብቸኛው ዘላቂ መፍትሄ ነው”

ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...