የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዓመቱን ማጠናቀቂያ ምክንያት በማድረግ ነገ ቅዳሜ ታህሳስ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ልዩ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ እንደሚካሄድ አስታወቀ።
በዚሁ ልዩ ጨረታ ላይ 150 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለገበያ እንደሚቀርብ ተገልጿል።
ባንኩ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ይህ ልዩ ጨረታ እየተካሄደ ያለው ባንኩ በየሁለት ሳምንቱ የሚያካሂደውን መደበኛ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ ተከትሎ ነው።
የጨረታው ዋና ዓላማም የዋጋ ንረትን መቆጣጠርና የሀገሪቱን የውጭ ኢኮኖሚ መረጋጋት ማረጋገጥ እንደሆነ ተጠቅሷል።
