አሜሪካ ከብቶች፣ ጫጩቶችና እንቁላሎች ለኢትዮጵያ ለመሸጥ ፈቃድ አገኘች

Date:

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን፣ ከአሜሪካ ከብቶችን፣ የአንድ ቀን ጫጩቶችና የሚፈለፈሉ እንቁላሎችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት የቀረበውን የገበያ ተደራሽነት ጥያቄ ማፅደቁን የአሜሪካ ግብርና መሥሪያ ቤት አስታወቀ።

ይህ ታሪካዊ የተባለለት የገበያ ፈቃድ የተረጋገጠው ታህሳስ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሆን፣ ይህም በሁለቱ አገራት መካከል ለዓመታት ሲካሄድ የቆየው የቴክኒክ ድርድር መጠናቀቁን የሚያመለክት መሆኑ ተጠቁሟል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የአሜሪካ የእንስሳትና ዕፅዋት ጤና ምርመራ አገልግሎት፣ ከኢትዮጵያ ግብርና ሚኒስቴርና በቅርቡ ደግሞ ከኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ጋር በቅርበት ሲሰራ መቆየቱ ተገልጿል።

የዚህ ትብብር ዋና ዓላማ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የእንስሳት ጤና የምስክር ወረቀቶችን ማዘጋጀት ሲሆን፣ አሁን ላይ ሰነዶቹ በመጽደቃቸው በህይወት ያሉ እንስሳትን ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ለማጓጓዝ የሚያስችል ሙሉ ህጋዊ መሠረት ተጥሏል ሲል ካፒታል ዘግቧል።

ቀደም ሲል አሜሪካ የበሬ ዘር እና ፅንስ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ፈቃድ አግኝታ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን የተገኘው ፈቃድ ግን በህይወት ያሉ እንስሳትን በቀጥታ ለማስገባት የሚያስችል በመሆኑ ለዘርፉ ትልቅ እመርታ ተደርጎ መወሰዱን ዘገባው ጠቁሟል፡፡

ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የአሜሪካ ዝርያዎች ወደ አገር ውስጥ መግባታቸው፣ አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች በትንሽ እንስሳት ቁጥር ከፍተኛ የወተትና የስጋ ምርት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል።

በተለይም በዶሮ እርባታ ዘርፍ ጥራት ያላቸው የአንድ ቀን ጫጩቶችና የሚፈለፈሉ እንቁላሎች እጥረት ለዘርፉ እድገት ትልቅ ማነቆ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...