የዲግሪ ሰርተፍኬት/ማስረጃ ህትመት በአንድ ማዕከል ሊከናወን ነው ተባለ

Date:

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የዲግሪ ሰርተፍኬት ህትመት በአንድ ማዕከል ሊከናወን መሆኑን አስታውቋል።

ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላለፈው ይህ መመሪያ በተቋማት የሚሰጡ ዲግሪዎች ህትመት ወጥ በሆነ መልኩና እንዲዘጋጁና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ታስቦ መሆኑ ተገልጿል።

በመሆኑም ተቋማቱ በዲግሪ የምስክር ወረቀቱ ላይ ሊካተትላቸው የሚፈልጉትን ሎጎ እና ሌሎች መካተት አለበት የሚሉትን ጉዳዮች እንዲያካትቱ ተነግሯል።

በተጨማሪም በየተቋማቱ በዚህ ዓመት የመውጫ ፈተና ወስደው ያለፉና ለምርቃት የተዘጋጁ ተማሪዎችን ስም ዝርዝር እንዲልኩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...