ቻትጂፒት ማስታወቂያ ማሳየት ሊጀምር ነው

Date:

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የሆነው ቻትጂፒቲ፣ ለአንዳንድ ተጠቃሚዎች ማስታወቂያ ማሳየት ሊጀምር እንደሆነ አስታውቋል።

የቻትጂፒቲ እናት ኩባንያ የሆነው ኦፕንኤአይ እንዳስታወቀው፤ የመጀመሪያ ሙከራውን በአሜሪካ ባሉ በነፃ በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ያደርጋል።

ቻትጂፒቲን ከፍለው የሚጠቀሙ ሰዎች ያሉ ሲሆን፤ ዝቅተኛ ዋጋው በወር 8 ዶላር ነው።

ኦፕንኤአይ እንዳለው፤ ሰዎች ቻትጂፒቲን በሚጠቀሙ ጊዜ አስፈላጊ የሚባሉ ማስታወቂያዎች ይመጡላቸዋል። ለምሳሌ ሜክሲኮ ውስጥ የሚጎበኝ ቦታ ጠቁመን ብለው የሚጠይቁ ሰዎች የሽርሽር ቦታዎች ማስታወቂያ ሊያዩ ይችላሉ።

ኩባንያው ተጠቃሚዎች ከቻትጂፒቲ ጋር የሚያወሩትን ነገር ማስታወቂያ ለሚያስነግሩ ድርጅቶች አሳልፎ እንደማይሰጥ ቃል ገብቷል።

አክሎም፤ ማስታወቂያ ያስፈለገው “በሚገኘው ገቢ ተጠቃሚዎቹን የበለጠ ለማገልገል” እንደሆነ ገልጿል።

ፋይናንሻል ታይምስ በአውሮፓውያኑ 2025 የመጀመሪያው 6 ወር ብቻ ኦፕንኤአይ 8 ቢሊዮን ዶላር ከስሯል ሲል ፅፏል። ቻትጂፒቲን ከሚጠቀሙት 800 ሚሊዮን ሰዎች መካከል 5 በመቶው ብቻ  ከፍለው እንደሚጠቀሙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...