እንኳን ለአስተርዕዮ ማርያም  አደረሳችሁ፣አደረሰን

Date:

ሞትን መቅመሷ እጅግ ይደንቃል

ለፍጥረት ሁሉ የምታዝን፣ ከርህራዬዋ ብዛት የተጠማን ውሻ በወርቅ ጫማዋ ያጠጣች፣ አባቶች ቢወዷት ሶልያና ያሏት፣ ተወዳጅ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በ64 ዓመቷ ጥር 21 ዐረፈች። የእረፍቷ ቀን መድረሱን ጌታችን ሲነግራት መሞት እንደማትፈልግ ነገረችው፡፡

እርሱም በሲኦል ያሉትን ነፍሳት አሳያት፤ እርሷም እነዚህ ነፍሳት ምህረትን እንዲያገኙ አንድ ጊዜ አይደለም ሰባት ጊዜ ልሙት አለችው፡፡ ነፍሷ ከስጋዋ የምትለይበት ጊዜ ሲደርስ ቅዱሳን ሐዋርያት ድንግል ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ቀረቡ፤ እጁዋን በላያቸው ዘርግታ ባረከቻቸው። በዚያን ጊዜ ጌታችን ንጽህይት ነፍሷን ከቅዱስ ስጋዋ ለይቶ ወሰደ።

የድንግል ማርያም ዕረፍት በመልአክት ዝማሬ፣ በብዙ ደስታ የታጀበ ስለነበር ሠርግ ነበር የሚመሥለው። በንጽህና አምላክን የወለደችው ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ ሁሉ ሰው ሞትን መቅመሷ እጅግ ይደንቃል፡፡

እንደሌላው ፍጥረት ሁሉ የድንግልን ሞት ተናግረን ዝም የምንል አይደለም፣ ይልቁንም ሞትን ድል እንዳረገው እንደ ልጇ እርሷም መነሳቷን እንመሰክራለን እንጂ። እንደ እመቤታችን እንደ ማርያም የአብ ማረፊያ የሆነ ማነው፡፡ እንደ እመቤታችን እንደ ማርያም የወልድስ ማደሪያ የሆነ ማነው፡፡ እንደ እመቤታችን ማርያም የመንፈስ ቅዱስ ቤት የሆነ ማነው፡፡

ከሰው ልጆች ከመቤታችን በቀር ኃጢአትንም ያልሰራ የለም፡፡ እመቤታችን ማርያም ከመላእክትና ከሰው ልጆች ሁሉ ይልቅ ንፅሕት ናት፡፡ የመቤታችን አሳብ እንደ አምላክ አሳብ ነው፡፡ የእመቤታችን ማርያም መልኳ እንደ አምላክ መልክ ነው፡፡

እመቤችን ማርያም ንጽሕት በመሆኑዋ አምላክን እንዲያድርባት አደረገችው፡፡ ገዳማውያን የንጽህና አብነት፣ የቅድስና ምሳሌ ነሽ እያሉ ያመሰግኗታል፡፡

እርሷም ዘወትር በበረከት ትጎበኛቸዋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391 ወይም አቢሲኒያ ባንክ 141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...