የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ለኢራን ህዝብ – “እኛ ከእናንተ ጋር ነን”

Date:

የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት ሮቤርታ ሜትሶላ፥ የኢራን መንግስት በተቃዋሚዎች ላይ የሚፈጽመውን ግድያ የሚያወግዝ የውሳኔ ሃሳብ ሐሙስ ዕለት ካጸደቁ በኋላ፣ የአውሮፓ ህግ አውጪዎች ለኢራን ህዝብ ጠንካራ የድጋፍ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ገለጹ።

ሜትሶላ በኤክስ ገጻቸው ላይ “ከአውሮፓ ፓርላማ ለኢራን ህዝብ የተላለፈ ጠንካራ፣ ግልጽና የማይናወጥ መልዕክት፡ እኛ ከእናንተ ጋር ነን” ሲሉ ጽፈዋል።

አክለውም፤ “ዛሬ የአውሮፓ ፓርላማ አባላት የኢራን አገዛዝ የሚፈጽመው አረመኔያዊ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆምና ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በከፍተኛ ድምፅ ጠይቀዋል” ብለዋል።

በተጨማሪም ሜትሶላ ከኢስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ኃይል ጋር የተያያዙ ማዕቀቦች በተግባር ላይ እንዲውሉ ጥሪ አቅርበዋል።

“በሽብርተኛው የኢስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ኃይል አባላት ላይ የተጣለው ማዕቀብ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆን አለበት። ምንም ዓይነት ክፍተት ወይም ሰበብ ሊኖር አይገባም” ሲሉ ጽፈዋል።

“ኢራን ነጻ ትወጣለች” ሲሉም አክለዋል፤ ፕሬዚዳንቷ፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...