ልጆች በስክሪን ላይ የሚያውሉት ጊዜ የቋንቋ ክህሎታቸው ይጨምር ይሆን ?

Date:

ብዙ ወላጆች የልጆቻቸው የስክሪን ሰዓት መብዛት ቢያሳስባቸውም አንዳንድ ጊዜ “ቋንቋ ይማራል” ፤ “ቃላቶችን ያቃል” የሚሉ አዘናጊ ግምቶችን ሲወስዱ ይስተዋላል።

የቋንቋ ተመራማሪዋ ሱዚ ዴንት ህፃናት ከመጽሐፍ ንባብ ይልቅ በዲጂታል ስክሪኖች (ስልኮችና ታብሌቶች) ላይ የሚያሳልፉት ጊዜ በመጨመሩ ምክንያት፣ የቃላት ክህሎታቸው አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ እየቀነሰ መሆኑን ትገልጻለች።

ከዚህ ይልቅ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አብረው እንዲያነቡ፣ እንዲጫወቱና የቃላት ጨዋታዎችን (Word Games) እንዲለማመዱ ትመክራለች።

ልጆች ከወላጆቻቸው ልምድ ነው የሚማሩት። እኛ በስልካችን ስራ ብንሰራም እንኳን ልጆቻችን የሚያዩት ግን በእነሱ ፈንታ ሌላ ነገር ላይ ትኩረታችንን ማድረጋችንን ነው።

የሚያነቡና የማያነቡ ልጆች መካከል ያለው ቋንቋ የመማር ልዩነት እየሰፋ መጥቷል። የሚያነቡ ልጆች አዳዲስ ቃላትን የመቅሰም ፍጥነታቸው በጣም ከፍተኛ ነው።

ልጆች አዳዲስ ቃላትንና ቋንቋ የሚማሩት ከእኛ ጋር በሚያደርጉት ንግግርና በንባብ ነው። ስልካችንን ትተን ከእነሱ ጋር የምናደርገው ውይይት ለዕድገታቸው ወሳኝ ነው
“ስትል ገልጻለች።

ዘጋርዲያን

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...