የኢትዮ-ቱርክዬ ስትራቴጂካዊ አጋርነት አዲስ ምዕራፍ

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቱርክዬ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ጋር በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል።

ይህ በሁለቱ ሀገራት በመሪዎች ደረጃ የተደረገው ምክክር በኢትዮጵያ እና በቱርክዬ መካከል ለዘመናት የዘለቀውንና በታሪክ የተፈተነውን ወዳጅነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ነው።

የመሪዎቹ ውይይት በስትራቴጂካዊ የትብብር መስኮች ላይ ትኩረት ያደረገ ጥልቅ የሐሳብ ልውውጥ ተካሂዶበታል።

ሁለቱ መሪዎች የሀገራቱን የጋራ ጥቅም የሚያስከብሩ አጋርነቶችን ይበልጥ ለማሳደግ ያላቸውን ፅኑ ቁርጠኝነት ዳግም አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመልዕክታቸው፥ ይህ ዘላቂ ግንኙነትና በስትራቴጂካዊ መስኮች የተጀመረው ጠንካራ ትብብር የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች የሚያስተሳስረውን ወዳጅነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ሙሉ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ይህ ታሪካዊ ግንኙነት ለሁለቱም ሀገራት ብልፅግና ብቻ ሳይሆን ለቀጣናዊ ሰላምና መረጋጋትም ያለው ፋይዳ የላቀ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...