ከሥጋ ወጪ ንግድ 61 ነጥብ 76 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝ

Date:

የኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሣሕሱ ሙሉ  እንደገለጹት በ2018 በጀት ዓመት ባሰፉት ስድስት ወራት ፍየል፣ በግ፣ በሬ፣ ግመል እና ከዕርድ ተረፈ ምርት  10 ሺህ 655 ቶን ለውጭ ገበያ ቀርቧል፡፡

በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ውጭ ገበያ ከተላከው ሥጋ እና የዕርድ ተረፈ ምርት 61 ነጥብ 76 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ሊገኝ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የሥጋና የዕርድ ተረፈ ምርት ዋነኞቹ መዳረሻ ገበያዎች የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች አና ሳዑዲ ዓረቢያ ቢሆኑም፤ ኳታር፣ ዮርዳኖስ፣ ኩዌት፣ ሆንግኮንግ፣ ቬትናም አና አንደ ናይጄሪያ እና ጋና ያሉ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት በተለይ የዕርድ ተረፈ ምርት የሚላከባቸው ገበያዎች አንደሆኑም ጠቁመዋል።

የሥጋና ተዋፅዖ ምርቶችን በጥራት አዘጋጅቶ መላክ የሚያስችሱ 12 የኤክስፖርት ቄራዎች ሥራ ላይ መሆናቸውን ገልጸው፤ የኤክስፖርት ቄራዎቹ በዓመት አስከ ሁለት መቶ ሺህ ቶን ሥጋ የመላክ አቅም አንዳላቸው ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...