12 የኢትዮጵያና ኤርትራ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ወታደራዊ አዛዦች በጀርመን በጦር ወንጀል ተከሰሱ

Date:

አንድ የቀድሞ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ሃላፊንና አንድ የቀድሞ የረድኤት ሠራተኛ በ12 የኢትዮጵያና ኤርትራ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ወታደራዊ አዛዦች በትግራይ “የጦር ወንጀል” እና “በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች” ፈጽመዋል በማለት ለጀርመን ዓቃቤ ሕግ ክስ አቀረቡ።

ከቀድሞ የአስተዳደሩ ሃላፊ እና የረድኤት ሠራተኛው በተጨማሪ ስምንት የትግራይ ተወላጆች ክሱን በጋራ አቅርበዉታል።

የወንጀሎቹ ሰለባና ወንጀሎቹ ሲፈጸም እማኝ የነበሩት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፣ የጀርመን ፌደራል ዓቃቤ ሕግ በወንጀሎቹ ላይ የምርመራ መዝገብ እንዲከፍትና በአገሪቱ ፍርድ ቤት ክስ እንዲመሠርት ጠይቀዋል።

ግለሰቦቹ አቤቱታውን ያቀረቡት፣ ሌጋል አክሽን ወርልድዋይድ በተሰኘ የሕግ ተቋምና ሌሎች ድርጅቶችና የሕግ ባለሙያዎች ድጋፍ ነው።

የጀርመን ዓቃቤ ሕግ በውጭ አገራት በተፈጸሙ ዓለማቀፍ አስከፊ ወንጀሎች ዙሪያ ምርመራ የማድረግ ሥልጣን አለው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...

የእግር ኳስ ዳኝነት በኢትዮጵያ

ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ግዮን መጽሔት :- እግር ኳስ...