“ብራንዴ ተሰርቋል” በሚል ጃምቦ ኮንስትራክሽን በጀንቦሮ ሪል እስቴት ላይ የ1 ሚሊዮን ብር ክስ መሰረተ

Date:

በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽንና የሪል እስቴት ኢንዱስትሪ ውስጥ ለሦስት አሥርተ ዓመታት ገደማ ስሙን የገነባው ጃምቦ ኮንስትራክሽን፣ አዲስ ወደ ገበያው በገባው ጀንቦሮ ሪል እስቴት ላይ የንግድ ምልክት ስያሜዬን ወስዶብኛል በሚል የ1 ሚሊዮን ብር የካሳ ክስ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መሰረተ።

ጃምቦ ኮንስትራክሽን ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው አቤቱታ፣ “ጀንቦሮ” የሚለው ስያሜ ከራሱ የንግድ ምልክት ጋር በድምፅ፣ በፊደላት አጻጻፍና በቃና ተመሳሳይነት ስላለው ደንበኞችንና ሚዲያን እያደናገረ ይገኛል ብሏል። ድርጅቱ ይህን ድርጊት “የብራንድ ነጠቃ” ሲል የገለጸው ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት 1 ሚሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብ ኪሳራ እንደደረሰበት ገልጿል።

በሌላ በኩል ጀንቦሮ ሪል እስቴት ባቀረበው መከላከያ፣ ክሱ የሕግ መሠረት የሌለው ነዉ ሲል ተከራክሯል። ድርጅቱ አክሎም “ጀንቦሮ” የሚለው ስም በጉራጌ ዞን የሚገኝ የመንደር ስም እንጂ ከሱዋሂሊው “ጃምቦ” ጋር ምንም ዓይነት የቋንቋ ዝምድና እንደሌለው ገልጿል። የሪል እስቴት ደንበኞች ከፍተኛ ገንዘብ አውጥተው ከመግዛታቸው በፊት የድርጅቱን ማንነትና ታሪክ በሚገባ የሚመረምሩ በመሆናቸው፣ በስም ተመሳሳይነት ብቻ ይሳሳታሉ የሚለው ክስ ተቀባይነት የለውም ሲልም ጀንቦሮ ተከራክሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢትዮጵያዊዉ የመጀመሪያው የአይን ሐኪም ዶክተር ጳውሎስ አረፉ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪም እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን...

ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች በዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር 3ኛ ወጡ

በካናዳ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ የተሳተፉት የኢትዮ...

ሁቲዎች የሳዑዲ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ገለጹ

የኢራን አጋር የሆኑት ሁቲዎች የሳዑዲ አራምኮ ጃዛን ነዳጅ ማጣሪያን...

በዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 2ኛ የወርቅ ሜዳሊያ አገኝች

በሴቶች 3 ሺህ ሜትር የተወዳደሩት  ዮርዳኖስ ጽጋብ እና ሽቶ...