በፋይናንስ ተቋማት የሚሰሩ  ሴቶች  ትብብር በመፍጠር በዘርፉ የጎላ ሚና እንዲጫወቱ ጉምቱ የዘርፉ ሴት ባለሞያዎች ጠየቁ

Date:

የባንክ፣ የኢንሹራንስ ዘርፍ ውስጥ እውቀቱም ልምዱም ያላቸው ሴቶች ቢኖሩም በአመራርነት ላይ ያሉት ግን አሁንም በጣት የሚቆጠሩ ናቸው ተብሏል።

ይህ የተባለው ሕብረት ኢንሹራንስ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን(March 8) ምክንያት በማድረግ  ባዘጋጀው የውውይት መድረክ ላይ ነው።

በመድረኩ የሕብረት ኢንሹራንስ  ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መሠረት በዛብህ፣ የወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ብሩታዊት ዳዊት አብዲ፣ የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ባለሙያ ሴቶች ማህበር  አባላት፣ የሕብረት ኢንሹራንስ የስራ ሀላፊዎችና የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሕብረት ኢንሹራንስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መሠረት በዛብህ “ሴቶች ወደ ከፍተኛ የአመራርነት ሚና ሲመጡ፤ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች መንገዱ ቀላል አይደለም”ብለዋል፡፡

“መንገዱ በብዙ ውጣ ውረድ የተሞላ፤ አባጣ ጎርባጣ በመሆኑ ምክንያት መንገዱን የጀመሩ ሴቶች ሁሉ ወደፊት አልመጡም፡፡
ምክንያቱም ወደ መዳረሻው ለመቃረብ መጠነ ሰፊ ትዕግስት፣ ባልተቋረጠ ትጋት ራስን ማብቃት፣ ፈተናን ለማለፍ የሚያስችል ቁርጠኝነት፣ ተግዳሮቶችን ለመጋፈጥ የሚረዳ ጥንካሬና በራስ መተማመን ብሎም ጥበብ የተሞላበት ውሳኔን ለመስጠት የሚያስችል ብልሃት ስለሚጠይቅ ነው”ሲሉ አስረድተዋል ፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በስራ አለም በቆዩባቸው ዓመታት ተስፋ ሊያስቆርጡ የሚችሉ በርካታ አጋጣሚዎችን እንዳሳለፉ ከህይወት ልምዳቸው እየጠቀሱ በዝግጅቱ ላይ ለተገኙ ሴት የኢንሹራንስና የባንክ ባለሞያዎች አስረድተዋል።

በዳይሬክተርነት፣ በቅርንጫፍ ሀላፊነት ሆነው በሚሰሩበት ወቅት ሃላፊ ሆነው ሳለ ሀላፊውን ጥሪልን ከሚለው ጀምሮ ለመወረፍ የሚቃጣቸው ደንበኞች እንዳጋጠሟቸው ተናግረዋል።

ነገር ግን ስራቸውን ጥንቅቅ አድርገው ስለሚሰሩ አሁን ላሉበት የዋና ስራ አስፈፃሚነት ደረጃ ድረስ መድረሳቸውን አስረድተዋል።

ከአላማ ለመድረስ ስለተገፋሁ ብሎ ምክንያት መደርደር አያስፈልግም ፣ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ሌላኛዋ በመድረኩ ልምዳቸውን ያጋሩት የወጋገን ኢንቨስትመንት ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ብሩታዊት ዳዊት በበኩላቸው በተለይ ብዙ የስራ ዘመናቸውን ባሳለፉባት አሜሪካ ጥቁር ፣ሴት፣ ስደተኛም በመሆናቸው ከህልማቸው እንዳይደርሱ ሊያደረጓቸው የሚችሉ አጋጣሚዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል።

አጋጣሚዎችን ለበጎ በመውሰድ ፣ በትምህርትና በእውቀት ከሚመስሏቸው ልምድ በመቅሰም ካሰቡት ከመድረስ ያገዳቸው እንደሌለ ተናግረዋል ።

ሁለቱ ጉምቱ ሴት የፋይናንስ ባለሞያዎች ሴቶች ከስራ መልስ ከማህበራዊ ህይወቱም ከሌላ ሌላውም ሰዓታቸውን አብቃቅተው በሞያና እውቀት ከሚመስሏቸው ጋር እንዲመሰክሩ፣ እንዲተባበሩ እና በዘረፉም ሴቶች ከፊት እንዲበዙ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ሴቶች እወቀቱም፣ ልምዱም እያላቸው ይህንን ሰራው ይህንን አሳካው የማለት ባህል ስለሌለ በባንክና ኢንሹራንስ ብዙ መሪዎች እንደማይታዩ ሲነገር ሰምተናል።

በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎችም የአንጋፊዎቹ የፋይናንስ ባለሞያዎች የስራና የህይወት ልምድ ብዙ ግንዛቤ ያገኙበት እንደሆነ ሲናገሩ ተሰምቷል።

አለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በዘሬው እለት ከሴት የፋይናንስ ባለሞያዎች ጋር ውይይት ያደረገው  ሕብረት ኢንሹራንስ  ሰኔ 30/2017 በተጠናቀቀው የሂሳብ ዓመት የኩባንያው የተከፈለ ካፒታል 1.34 ቢሊዮን ብር፣ ጠቅላላ ሃብቱ ደግሞ ከ6 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱን መናገሩ ይታወሳል፡፡

ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...