በመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተው ጦርነት “በቀጣናው ለሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕፃናት እሰቃቂ ነው” ሲል የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት ኤጀንሲ (ዩኒሴፍ) አስታወቀ።
አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21/2018 ዓ.ም. ኢራን ላይ ጥቃት ከከፈቱበት ዕለት አንስቶ ከ1,100 በላይ ሕጻናት ጉዳት ወይም ሞት እንደደረሰባቸው ዩኒሴፍ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
መግለጫው አክሎም ይህ መረጃ በኢራን የተገደሉ 200፣ በሊባኖስ 91፣ በእስራኤል አራት እንዲሁም በኩዌት አንድ ሕፃናትን ያጠቃልላል።
ዩኒሴፍ “የሕፃናትን መገደል እና የአካልጉዳት ማድረስ ወይም ሕጻናት የሚገለገሉባቸውን አስፈላጊ አገልግሎቶች ማውደም እና መቋረጥ ምንም ምከንያት የሚቀርብበት ነገር አይደለም “ ብሏል።
ድርጅቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተዋጊ አካላት “ጦርነቱን ቆሞ ወደ ዲፕሎማሲ ድርድር እንዲመጡ” ያቀረቡትን ጥሪ በድጋሚ እንደሚያቀርብ አስታውቋል።
በተጨማሪም በጦርነት የሚሳተፉ አካላት “በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ፣ ይህም ሕፃናትን የሚጎዱ ፈንጂዎችን ከመጠቀም መቆጠብን ጨምሮ፣ የጦር መሳሪያዎችን በመምረጥ ረገድ ሁሉንም አስፈላጊ ጥንቃቄዎች እንዲወስዱ” ጥሪ አቅርቧል።
BBC
