የመምህር ዘላለም ወንድሙ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሥርዓተ ቀብሩ በክብር ተፈጽሟል።
በሽኝት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሃይማኖት አባቶች፣ ደቀ መዛሙርቱና ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ከመስቀል አደባባይ እስከ መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ ሐዘንና አክብሮት ተሸኝቷል።
በዚህ መሪር ሐዘን ወቅት የታላቁን መምህር ሕይወትና አገልግሎት የሚዘክሩ ቅዱሳን ቃላት ተደምጠዋል፦
ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው።&
(መዝሙር 116፥15)
ይሞታል በልቡም የሚያስብ የለም& ጻድቅ ከክፉ ነገር ፊት ተወግዶአልና። ወደ ሰላም ይገባል& (ኢሳይያስ 57፥1-2)
ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን (ምስጉኖች) ናቸው& ከመከራቸው ያርፉ ዘንድ ሥራቸውም ይከተላቸዋል።& (ራዕይ 14፥13)
የማይሞት ስም እና ሥራ
የመምህር ዘላለም ሞት የምድራዊ ድካም ፍጻሜ እንጂ የጥበብ
በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ታሪክ ውስጥ እንደ ማኅተም የታተመው ስሙ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር ይኖራል።
ሞት የፍጻሜ ጥፋት ሳይሆን ከምድራዊ ድካም አርፎ ከፈጣሪ ጋር ለመገናኘት የሚደረግ የሽግግር ጉዞ ነው።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ የጥበብ ቤተሰብ መጽናናትን እንመኛለን።
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያሳርፍልን!
