ዩቲዩብ በAI  የሚፈጠሩ የሐሰት ምስሎችን ለማስወገድ የሚያስችል አሰራር ሊጀምር ነው

Date:

ዩትዩብ የግለሰቦችን ድምፅና መልክ በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) አስመስለው የሚሠሩ የሐሰት ቪዲዮዎችን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የሚያስችል አዲስ መከላከያ ይፋ አደረገ።

ይህ አገልግሎት በተለይ ጋዜጠኞች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የፖለቲካ ዕጩዎች በማንነታቸው ተመሳስሎ የሚሰራጭባቸውን የተጭበረበረ መረጃ በቀጥታ እንዲያስወግዱ ዕድል ይሰጣል።

ኩባንያው ይህን የጀመረው በAI አማካኝነት የሚፈጠሩ የሐሰት ምስሎች በሰዎች ስም እና በሀገራት ደህንነት ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ለመከላከል መሆኑን ገልጿል።

ይህንን ጥበቃ ለማግኘት የሚፈልጉ ግለሰቦች የራሳቸውን ትክክለኛ ቪዲዮ ቀርጸው ዩትዩብ ባዘጋጀው ቅጽ ላይ መመዝገብይኖርባቸዋል።

አንዴ ማንነታቸው ከተረጋገጠ በኋላ፣ ዩትዩብ የእነሱን መልክና ድምፅ ተጠቅመው በAI የተሰሩ ቪዲዮዎችን ዝርዝር ለአመልካቾቹ ያቀርባል።

ተጠቃሚዎችም እነዚህ ቪዲዮዎች ከገጹ ላይ እንዲነሱላቸው መጠየቅ የሚችሉ ሲሆን፣ ኩባንያውም ጥያቄው የቀረበባቸውን ምስሎች ወዲያውኑ እንደሚያስወግድ አረጋግጧል።

ይህ አዲስ አሰራር በአሁኑ ወቅት ትኩረቱ ታዋቂ ግለሰቦች ላይ ቢሆንም፣ ዩትዩብ በቀጣዮቹ ዓመታት ተደራሽነቱን በማስፋት ማንኛውም ሰው ማንነቱን ከAI ወረራ እንዲከላከል ለማድረግ አቅዷል።

የቴክኖሎጂው ዓለም በAI እያደገ በመጣ ቁጥር፣ ዩትዩብ ይህንን እርምጃ መውሰዱ የእውነትና የሐሰት ልዩነት እንዳይጠፋ ትልቅ እገዛ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...