የፊልም ዳይሬክተር ጳውሎስ ረጋሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

Date:

የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ አንዱን ድንቅ ባለሙያውን አጥቷል።

በፊልም ዳይሬክተርነቱ፣ በሙዚቃ ቀማሪነቱና በፖስት ፕሮዳክሽን (Post-production) ሊቅነቱ የሚታወቀው ጳውሎስ ረጋሳ ፣ ቅዳሜ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

​ጳውሎስ በተለይ “አሸንጌ” የተሰኘውን ድንቅ ፊልም ለታዳሚ በማቅረብ የሚታወስ ባለሙያ ነው።

​ለብዙ የዘርፉ ባለሙያዎች የሲኒማ ጥበብ መምህር፣ በተግሳጽና በምክር ያሳደገ ታላቅ ወንድም እንዲሁም ነገሩ ሁሉ ፊት ለፊት የሆነ እውነተኛ ባለሙያ ነበር።

​ከዳይሬክተርነት ባለፈ በሙዚቃ ቅንብርና በፊልም ቴክኒክ ሥራዎች ላይ የነበረው ተሰጥኦ ለኢትዮጵያ ሲኒማ ዕድገት ትልቅ አሻራ ጥሎ አልፏል።

​ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹና ለመላው የኪነጥበብ ቤተሰብ መጽናናትን እንመኛለን።

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ፦
መቼ እንደሚከናወን አስከሬኑ ከሕንድ ሲመጣ የምናሳውቅ ይሆናል።

የጥበብ ሰው ጳውሎስ ረጋሳ ነፍስ ይማር!

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...