የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ለሰላም ሲባል የኒውክሌር ፕሮግራሟን ለመተው ልትስማማ እንደምትችል ተናገሩ።
“ነገ ጠዋት፤ በእነርሱ የሆነ ሰዓት ላይ፣ ለመገንባት 10 ቢሊዮን ዶላር የወጣበትን ትልቁን የኤሌትሪክ ማመንጫ ፋብሪካቸውን ለማፈንዳት እየጠበቅን ነበር” ሲሉ ተናግረዋል።
“በጣም ጥሩ ነበር፤ የገንዘብ እጥረት አልነበረም፤ በአንድ ተኩስ ይወድማል፤ ይፈራርሳል። ለምን ይህን ይፈልጋሉ?
“እነርሱ ናቸው የደወሉት፤ እኔ አልደወልኩም። እነርሱ ደወሉ። ስምምነት ላይ መድረስ ፈልገዋል” ሲሉ ተናግረዋል።
“እኛ ከስምምነት ላይ ለመድረስ በጣም ፈቃደኞች ነን። ጥሩ ስምምነት መኖር አለበት፤ እና ሌላ ጦርነት ሊኖር አይችልም፤ የኒውለክሌር ጦር መሣሪያ አይኖርም።
“ከእንግዲህ በኋላ የኒውክሌር ጦር መሣሪያ አይኖራቸውም። በዚያ ይስማማሉ። ያለዚያ ግን ስምምነት አይኖርም” ሲሉ ተናግረዋል።
