ጃፓን ከብሔራዊ የመጠባበቂያ ነዳጅ ክምችቷን ልትጠቀም ነው

Date:

የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካኢቺ አገራቸው ሐሙስ ዕለት ከብሔራዊ የነዳጅ መጠባበቂያ ክምችቷ እንደምትለቅ አስታውቀዋል።

ጃፓን እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው የነዳጅ አቅርቦት እጥረት ስጋት እያደገ በመምጣቱ ነው።

አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጦርነት መክፈታቸውን ተከተሎ ቴህራን ሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥን በመዝጋቷ የዓለም የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ዋጋ አሻቅቧል።

ታካኢቺ በኤክስ ገጻቸው ላይ “ከሐሙስ ጀምሮ ከብሔራዊ ክምችታችን ነዳጅ መልቀቅ እንጀምራለን” ብለዋል።

ጃፓን ባለፈው ሳምነት “ለአገሪቱ በአጠቃላይ የሚያስፈልጋትን” ነዳጅ ለማቅረብ በሚል ከግል ክምችቶቿ መጠቀም ጀምራለች። ጃፓን የምትጠቀመው 95 በመቶ ነዳጅ የሚመጣው በሆርሙዝ ወሽመጥ ኩል ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ማክሰኞ በእስያ የአንድ በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት ዋጋ ከ100 ዶላር በላይ እየተሸጠ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በችኮላና በጥድፊያ” የሚዘጋጁ ህጎች፣ በህግ አወጣጥ ስርዓቱ ላይ አለመረጋጋት እየፈጠሩ ነዉ

በኢትዮጵያ የህግ አወጣጥ ሂደት ውስጥ ተደጋጋሚ ማሻሻያዎች፣ የአዋጅ መሻሮችና...

ኢትዮጵያ ሆቴል ሊፈርስ ነው

ታሪካዊው ኢትዮጵያ ሆቴል ሙሉ በሙሉ ሊፈርስ እንደሆነ ፎርቹን ጋዜጣ...

የክልል ልዩ ኃይል ይፍረስ ፣ ሀገር አቀፍ ሚሊሻ ይደራጅ የሚሉ አጀንዳዎች ቀርበዋል

በፌደራል ከተሞች ጉዳይ ጥላ ውስጥ የወደቀው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ፤...

ኢትዮጵያዊዉ የመጀመሪያው የአይን ሐኪም ዶክተር ጳውሎስ አረፉ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪም እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን...