አምዞን እና ዴልታ አየር መንገድ የሳተላይት ኢንተርኔት ስምምነት ተፈራረሙ

Date:

የአማዞን ኩባንያ የሳተላይት ኢንተርኔት ክፍል  ከዴልታ አየር መንገድ ጋር በ500 አውሮፕላኖች ላይ የዋይ ፋይ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል።

እ.ኤ.አ. በ2028 አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ስምምነት፣ አማዞን በዘርፉ ቀዳሚ ከሆነው የኢሎን ማስክ ‘ስታርሊንክ’ ጋር ያለውን ፉክክር ይበልጥ እንደሚያፋጥነው ተነግሯል።

ስታርሊንክ በአሁኑ ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ሳተላይቶችን ወደ ህዋ በማምጠቅ የገበያ የበላይነቱን ቢይዝም፣ አማዞን ግን ከዴልታ በፊት ከጄት ብሉ ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት የገበያ ድርሻውን ለማስፋት በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

ኩባንያው ከኤፕሪል 2025 ጀምሮ 214 ሳተላይቶችን ወደ ህዋ ያመጠቀ ሲሆን፣ በሚቀጥሉት 12 ወራት ውስጥ ከ20 በላይ መንኮራኩሮችን በመጠቀም የማምጠቅ አቅሙን እጥፍ ለማድረግ አቅዷል።

ዴልታ አየር መንገድ አማዞንን ለዚህ አገልግሎት የመረጠውም ቀደም ሲል ከአማዞን ዌብ ሰርቪስ ጋር ባለው ጠንካራ የክላዉድ ስሌት ሥራ ትብብር ምክንያት እንደሆነ ገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...