አርሰናል ከቦርንማውዝ በጉጉት የሚጠበቅ ጨዋታ

Date:

በ32ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ቀን 8 ሰዓት 30 ላይ አርሰናል በኢምሬትስ ቦርንማውዝን ያስተናግዳል፡፡

የሊጉ መሪ አርሰናል በሊጉ አምስተኛ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት እና መሪነቱን ለማጠናከር ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡

ያለፉትን አምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለው ተጋጣሚው ቦርንማውዝ በበኩሉ÷ ወደ ድል ለመመለስ ብርቱ ፉክክር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አርሰናል የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ማንቼስተር ሲቲ እስኪጫወት ድረስ የነጥብ ልዩነቱን ወደ 12 ከፍ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት 30 ላይ ሊቨርፑል በአንፊልድ ሮድ ፉልሃምን ይገጥማል፡፡

ሊቨርፑል በሊጉ ከሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል አልባ ጉዞ በኋላ ወደ ድል ለመመለስ ይፋለማል፡፡

ተጋጣሚው ፉልሃም በበኩሉ÷ ተከታታይ ድሉን ለማሳካት የሚያደርገው ፉክክር ተጠባቂ ነው፡፡

አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ በርንሌይ ከብራይተን እንዲሁም ብሬንትፎርድ ከ ኤቨርተን ሌሎች በሊጉ የሚደረጉ የዛሬ ጨዋታዎች ናቸው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...