ለጅቡቲ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ተከናወነ

Date:



ለጅቡቲ ድንበር ተሻጋሪ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክት 12 ነጥብ 2 ሜጋ ዋት ተጨማሪ የኤሌክትሪክ ኃይል መሠረተ ልማት ዝርጋታ መከናወኑን  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሰታወቀ።

የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቱ ዝርጋታ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ ሲከናወን ቆይቷል። በመጀመሪያው ምዕራፍ 8 ሜጋዋት ኃይል፣ 36 ኪሜ የመስመር ዝርጋታ እንዲሁም ስምንት ባለ1250 ኬቪኤ ትራንስፎርመር ተከላ ተከናውኗል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና ኦንያድ የተሠኘው የጅቡቲ ውኃ ፕሮጀክት ባቀረቡት ተጨማሪ ኃይል ጥያቄ ሁለተኛው ምዕራፍ ሊሰራ ችሏል፡፡

ለውኃ ፕሮጀክቱ 12 ነጥብ 2 ሜጋ ዋት ተጨማሪ ኃይል ከአዲጋላ ሰብስቴሽን 8 ሜጋዋት በ1250 ኬቪኤ ስምንት ትራንስፎርመሮች፤ ቀሪው 4 ነጥብ 2 ሜጋ ዋት በ28 ባለ500 ኪቪኤ፣ 315 ኬቪኤና 400 ኪቪኤ ትራንስፎርመሮች ኃይል እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡

በሁለተኛው ምዕራፍ 46 ኪሜ መስመር ዝርጋታና 28 ትራንስፎርመሮች የማስቀመጥ ስራ ተሰርቷል፡፡

በሁለቱም ምዕራፍ በተከናወኑት የመስመር ዝርጋታ የትራንስፎርመር ማስቀመጥ፣የቆጣሪ መግጠም ስራዎች በአጠቃላይ 82 ኪ.ሜ መስመር ዝርጋታ፣ 36 ትራንስፎርመሮች እንዲቀመጡ ተደርጓል፡፡

የአካባቢውን በርሃማ የአየር ፀባይ በመቋቋም ስራውን በስኬታማነት ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት የፕሮጀክቱ የሁለተኛው ምዕራፍ ሥራ ተጠናቆ ርክክብ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።(ኢ ፕ ድ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...