በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው አደገኛ አካሄድ ብዙ ቀውስ እንደሚያስከትል በተከታታይ ሲገለጽ ቆይቷል።
ከዛም ባለፈ ይህ የተሳሳተ አካሄድ በህዝባችን ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ቀውስና አደጋ ግምት ውስጥ በማስገባት አደጋውን በልኩ ተረድቶ ምክክርና መግባባት እንዲደረግበት ተደጋጋሚ ጥሪ ቀርቧል።
ሆኖም “ተመርጫለሁ” ብሎ በቅርቡ ያወጀው አካል ጥሪውን ችላ በማለት ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም በሰራዊት ጥብቅ ጥበቃ ተደርጎለት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ መሰብሰቢያ ኣዳራሽ ውስጥ “የካቢኔ ስብስባ ጀምሬያለሁ” ብሎ በምስል የተደገፈ መረጃ ይፋ አድርጓል።
ይህ ድርጊት የቀጣዩ አደገኛ ምዕራፍ መጀመር ይፋ የሆነበት አጥፊ እንቅስቃሴ ስለሆነ፣ ይህን ህገወጥ ተግባር ተከትሎ በህዝባችን ላይ ለሚደርስ ሁሉን አቀፍ ጥፋትና አደጋ ተጠያቂው ራሱ በጉልበት የአስተዳደሩን ስልጣን ለመያዝ እየሞከረ ያለው አካል መሆኑን ለመግለፅ እፈልጋለሁ።
ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል)
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት
ሚያዝያ 30/2018 ዓ.ም
መቐለ
