አሐዱ ባንክ በዲጂታል ኪራይ አሰባሰብ ዙሪያ ሥልጠና ሰጠ

Date:

አሐዱ ባንክ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ) የሕንጻዎች አስተዳደር ኤጀንሲ ያበለጸገውን የዲጂታል ኪራይ አሰባሰብ ሥርዓት  በይፋ ጀምሯል።


የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ቤቶች እና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ኤጀንሲ ይዞት የተነሣውን የዲጂታል አስተዳደር ግብ እውን ለማድረግ አሐዱ፡ባንክ ያበለጸገው ይህ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ሥርዓት፤  ብፁዕ አባታችን አቡነ ሳሙኤል  በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የክርስቲያናዊ ተራድኦ ልማት ኮሚሽን እና ቤቶችና ሕንጻዎች አስተዳደር ልማት ኤጀንሲ የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ  በተገኙበት ዝርዝር ገለጻ ተደርጎበታል።

ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ሥርዓት ተከራዮች የኪራይ ክፍያቸውን በሞባይል ባንኪንግ በቀላሉ እንዲፈጽሙ የሚያስችል ሲሆን፣ የመክፈያ ጊዜ ማስታወሻና የክፍያ ምስጋና መልዕክቶችን በራሱ ይልካል።

በተጨማሪም የክፍያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን ተከራዮች የመቆጣጠር አቅም ያለው ሲሆን፣ ለቤተ ክርስቲያኗ ቀልጣፋ የፋይናንስ ቁጥጥርና ግልጽነትን ያሰፍናል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...