አሜሪካ ለኢራን ብሔራዊ ቡድን ቪዛ ፈቀደች

Date:

አሜሪካ ለዓለም ዋንጫ ላለፈው የኢራን ብሔራዊ ቡድን ስፖርተኞችና የቡድን አባላት ቪዛ መስጠቷን አስታወቀች። የኢራን ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታውን በሎስ አንጀለስ ከተማ ከኒው ዚላንድ ጋር እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ግን ውሳኔውን ያስተላለፉት ጥብቅ ጥንቃቄ በማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።

“የኢራን ብሔራዊ ቡድን ሥርዓቱን በመበዝበር አሸባሪዎችን ወደ አሜሪካ እንዲያስገባ አንፈቅድም” ሲሉ ባለሥልጣናቱ ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢራን እግር ኳስ ፌደሬሽን ስለ ቪዛው መሰጠት እስካሁን በይፋ የሰጠው መግለጫ የለም። ይህ ክስተት በዓለም ዋንጫ ታሪክ ውስጥ አንዲት አስተናጋጅ አገር በጦርነት ውስጥ ከምትገኝ አገር ጋር ያላትን የፖለቲካ ውጥረት ወደ ጎን በመተው ብሔራዊ ቡድኑን ስትቀበል የመጀመሪያው ያደርገዋል፤ ይህም በስፖርቱ ዓለም ከፍተኛ ትኩረት ስቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...