የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ከ40 ዓመታት በኋላ የነዳጅ ምርት ማጓጓዝ ጀመረ

Date:

​የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት (ኢባትሎ) ሀገሪቱ ከውጭ የምታስገባውን የነዳጅ ምርት የማጓጓዝ ሥራ ከ40 ዓመታት በኋላ በድጋሚ መጀመሩን አስታወቀ። ተቋሙ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ከናይጄሪያ የተገዛን የኤቪዬሽን (የአውሮፕላን) እና የናፍጣ ነዳጅ በቻርተር መርከቦች ማጓጓዝ ችሏል።

​በሆርሙዝ ባህር ሰርጥ አካባቢ በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት በተፈጠረው የትራንስፖርት መስተጓጎል እና በሀገር ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የነዳጅ ፍላጎት ለማሟላት መንግሥት የነዳጅ ግዢ ምንጮቹን እያሰፋ ይገኛል።

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለበትን ከፍተኛ የአውሮፕላን ነዳጅ ፍላጎት ለማሟላትና አማራጭ መስመሮችን ለመጠቀም ከናይጄሪያው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ ግዢ ተፈጽሟል።

​ኢባትሎ እንዳስታወቀው ተቋሙ መንግሥት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ በመጠቀም 120 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአውሮፕላን እና የናፍጣ ነዳጅ በሦስት ተከታታይ ጉዞዎች ወደ ጅቡቲው ሆራይዘን ተርሚናል ማጓጓዝ ችሏል። ይህ ስኬት ነዳጅ የማጓጓዝ ልምድ ላልነበረውና “አቅም የለውም” ተብሎ ለሚታሰበው የሎጂስቲክስ ተቋም ትልቅ የሥራ ክንውን መሆኑን አስምሮበታል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...