ውይይቱ ወዳጃዊ እና ግልጽ እንደነበር እንዲሁም ለ55 ደቂቃዎች መቆየቱን የክሬምሊን ረዳት ኡሻኮቭ አስታውቀዋል።
ፑቲን ለትራምፕ 80ኛ ዓመት የልደት በዓል የእንኳን አደረሰዎት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች በሁለቱ ሀገራት ተወካዮች መካከል ሊደረጉ ስለሚችሉ ግንኙነቶችም ተወያይተዋል።
በውይይቱ የተደረጉ ቁልፍ ንግግሮች፦
▪️ ትራምፕ በፑቲን የስልክ ጥሪ እጅግ መነካታቸውን በመግለጽ፤ ፑቲን ወደ ዋይት ኋውስ በመደወል የመጀመሪያው የውጭ ሀገር መሪ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
▪️ ዊትኮፍ እና ኩሽነር በቅርቡ በሩሲያ ይፋዊ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡
▪️ ሁለቱ መሪዎች በዋና ዋና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች እና በአሜሪካ-ሩሲያ ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል፡፡
▪️ ትራምፕ በዩክሬን ያለውን ግጭት የማስቆም አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
▪️ ትራምፕ ለቀውሱ እልባት ለመስጠት በአውሮፓ ሀገራት እና በኪየቭ ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
▪️ በውይይቱ ወቅት የአሜሪካ እና የኢራን የመግባቢያ ስምምነት ጉዳይም ተነስቷል፡፡
▪️ ትራምፕ የአሜሪካ እና የኢራን ስምምነት መቃረቡንና በቅርቡ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል ገልጸዋል፡፡
▪️ ፑቲን በኢራን ዙሪያ ያለው ውጥረት እየረገበ በመምጣቱ የተሰማቸውን እርካታ አጋርተዋል።
