በሀገራችን የባህል ሙዚቃ ዘርፍ ታዋቂነትን ያተረፈውና በብዙሃን ዘንድ ሰሜ ባላገሩ”እየተባለ በሚጠራው ተወዳጁ ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ህልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን።
ባደረበት የድንገተኛ ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዳ የቆየው ድምጻዊው፣ በተወለደ በዛሬው ዕለት (ሰኔ 8 ቀን 2018 ዓ.ም) በተደረገለት የህክምና ክትትል ህይወቱ ማለፉን የቅርብ ቤተሰቦቹ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያን ባህል፣ ወግና ታሪክ የሚያንጸባርቁ በርካታ የሙዚቃ ስራዎችን ለአድማጮች ያበረከተው ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው፣ በሙዚቃው ኢንደስትሪ ውስጥ የራሱን ደማቅ አሻራ ጥሎ ማለፍ የቻለ ከያኒ ነበር።
ድምጻዊ ሰማኸኝ በለው ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት እንደነበር ከቤተሰቦቹ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለወዳጅ ዘመዶቹ እንዲሁም ለመላው የኪነ-ጥበብ አድናቂዎቹ በሙሉ መጽናናትንና ብርታትን ይመኛል። ፈጣሪ ነፍሱን በገነት ያኑራት።
