‹‹ሃገረ ትግራይ›› በዘመናት መነፅር ሲታይ

Date:


(አጭርዳሰሳ) በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ)

የመጽሐፉርዕስ፡- ሃገረ ትግራይ

የመጽሐፉ ዓይነት፡- ታሪክ ወፖለቲካ መጽሐፉ
የታተመበት ጊዜ፡- የካቲት 2018 ዓ.ም የመጽሐፉ የገፅ ብዛት፡- 316 ገፅ የመጽሐፉ ዋጋ፡- 600 ብር (25 USD)

እንደመግቢያ


ግዮን መጽሔት :- አዲስ መጽሐፍ ነው ፤ “ሃገረ ትግራይ”፡፡ ደራሲው ደግሞ ሙሉጌታ አረጋዊ ነው፡፡ ሙሉጌታ፤ ከዚህ ቀደም “ዲቪ ሎተሪ” በ1993 ዓ.ም፣“አብራክ” በ2011 ዓ.ም፣ “ሕግ ሲዳኝ” በ2016 ዓ.ም የተሰኙ ሦስት መጻሕፍቶችን ለሕትመት አብቅቷል፡፡

2015 ዓ.ም ጀምሮበአርትስ ቴቪ የሚታየውን “በሕግ አምላክ” ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማም የፃፈልን ነው፡፡ ይህ “ሃገረ ትግራይ” የተሰኘው መጽሐፉአራተኛ ሥራው መሆኑ ነው፡፡

ሙሉጌታየሕግ ሰው ፤ ለዚያውም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር፡፡ በሌላ አነጋገር ሀገሪቷ ካፈራቻቸው ጉምቱ የሕግ ሰዎች አንዱነው፡፡ ለዚህም ይመስለኛል ባበረከተልን የጽሁፍ ሥራዎቹ “ሕግ”ን ዋነኛ ማጠንጠኛው ያደረገው፡፡

ይህኛውም “ሃገረ ትግራይ” መጽሐፉእንደዚያው ነው፤ ሃገራዊ ታሪክን ይተነትንበታል፤ ፖለቲካችንን ይቃኝበታል፤ ሕጋዊ ሙግትም ያቀርብበታል፡፡ ለዚህ ነው የመጽሐፉንዓይነት “ታሪክ ወፖለቲካ” ነው ለማለት የተገደድኩት።

፩

የሙሉጌታ“ሃገረ ትግራይ” መጽሐፍ በስምንት ምዕራፍ የተከፈለ ነው፡፡ የመጀመሪያ ሦስቱ ምዕራፎች የኢትዮጵያን ታሪክ የቃኘበት ነው፡፡ ይህንንምየሚያደርገው የኢትዮጵያ ታሪክ በጽሑፍ መስፈር የጀመረበት ወቅት ነው ተብሎ ከሚታመነው ከዳዕማት ሥርወ መንግሥት አንስቶ ነው፡፡ከዚያምየኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በሃገር ምሥረታ ላይ ያላትን ሚና፣ የእስልምናን ወደ ኢትዮጵያ መግባት፣ የሰለሞናዊውን ሥርወ መንግሥትመከሰት እስከ ፍፃሜው ድረስ ያስቃኘናል፡፡

ደራሲውበየምዕራፉ ውስጥ በንዑስ ርዕሶች እየከፋፈለ የዘመን አዝማናት በርካታ ታሪኮችን ያወጋናል፡፡ የቃላት አጠቃቀሙ፣ የዐረፍተ ነገርአሰዳደሩ ቅልብጭ ቅልብጭ ማለት የተዋጣለት ነው፡፡ ይህም የታሪክ አተራረኩን ጣፋጭ እና ውብ አድርጎታል፡፡

፪

የሚቀጥሉትምዕራፎች የደርግ፣ የኢሕአዴግ እና የአሁኑን ዘመነ ብልፅግና ፖለቲካዊ ሁኔታ ከታሪክ ጋር እያሰናሰነ የሚያስቃኝበት ነው፡፡ እናምሕጋዊ ሙግቶችን እያስከተለ፣ በታሪክ መነፅር ውስጥ የኢትዮጵያን እና የሃገረ ትግራይን ማግኔታዊ ጥምረት ያሳየናል፡፡

ለዚህም ነው ክጥንተ ጥንት የኢትዮጵያ ታሪክ ተነስቶ የሚንደረደረው፡፡ሙሉጌታበትረካው፣ “አክሱም፣ ኢትዮጵያዊ
ያን የጠንካራ ብሔራዊ ኩራትና የዘመናት ታሪክ ባለቤት በማድረግ የራስ መተማመኛ ስሜት አስፍናለች”(ገፅ 25) ይለናል፡፡

እናም በኢትዮጵያ ሃገረ መንግሥት ምሥረታ ውስጥ ትግራይ ከፍ ያለ ሚና እንደነበራት ይነግረናል፡፡ በሰለሞንሥርወ መንግሥት ውስጥ የትግራይ ሚና የላቀ እንደነበር ይተርከናል፡፡ ክብረ ነገሥትን በመፃፍ የንግስና መስመርን በመቀየስ “ኢትዮጵያንከጁዶ ክርስትና ጋር በማጣመርና ብሔራዊ ተረክ በመፍጠር” (ገፅ 33) ፍትሐ ነገሥትን በማጋጀት ረገድ የትግራይ አስተዋፅኦ (ገፅ36)ን በማመላከት፣ ትግራይን ከኢትዮጵያ መነጠል እንደማይቻል ያመላክተናል፡፡

፫

እንዲህ እንዲህ እያለ በበርካታ የታሪክ ማጣቀሻዎች አስረጅ እያቀረበ የሚዘልቀው ሙሉጌታ (ደራሲው)፣ የትግራይ መሪዎች እና የኢትየጵያ መንግሥታት(ነገሥታት) ግንኙነት ፍፁም የሰመረ እንዳልነበረ ይነገራል፡፡

የባላባቶች ኩርፊያና አመፅ እንግዳ እንዳልነበር የሚጠቅሰው ሙሉጌታ፣በሺህ ሺህ ዘመናት በጋራ በተጋመደ ታሪክ ውስጥ የፈለገ መከፋት ቢኖር ትግራይ ወይም የትግራይ መሪዎች አንድም ጊዜ ከኢትዮጵያ ስለመነጠል(ስለመገንጠል) አስበው እንደማያውቁ ይነግረናል፡፡

ይህ ነው የመጽሐፉ ዋና አስኳል፡፡ እዚህ ላይ ከመጽሐፉ ቃል በቃል እንጥቀስ፡-“ምኒሊክኤርትራን ለጣሊያን ሲተውለት የታላቋ ትግራይ ሕዝብ የራሱን ነጻ ሃገር መመሥረት ይችል ነበር፡፡ አፄ ኃይለሥላሴ ከስደት ሲመለሱምበወቅቱ የትግራይ ትግርኚ ሃሳብ ሲያቀነቅን በነበረው በእንግሊዝ ረዳትነት ነፃ ሃገር መመሥረት ይቻል ነበር፡፡

የወቅቱ ፖለቲከኞችግን መገንጠልን አልመረጡም፡፡“ ተጋሩ ከኢትዮጵያ መገንጠል የሚያስችላቸውን ኮስታራ ሙከራ
ምንግዜም አድርገው አያውቁም፡፡ ሁሌ ለኢትዮጵያ ሲቆሙ ነው የሚታዩት፡፡ ሕወሓትሳይቀር ትግሉን ትግራይን ነፃ ለማውጣት ነው በሚል ጀምሮ ትግሉን በሚያሳካበት ሰዓት ላይ ሲደርስ አላደረገውም፤ የኢትዮጵያ ምትሐታዊመስህብ ከኢትዮጵያ ርቆ እንዲሄድ አልፈቀደለትምና፡፡” (ገፅ182
)

፬

ሙሉጌታ “የኢትዮጵያ ምትሃታዊ መስህብ ከኢትዮጵያ ርቆ እንዲሄድ አልፈቀደለትም” ብሎ በደፈናው አያልፈውም፡፡ ምክንያቱም “ሃገረ ትግራይ”ን መመሥረት አለብን የሚል ሃሳብ ያላቸው ወገኖች ብቅ ብለዋልና፡፡ይሁንእንጂ ሙሉጌታ “(የአሁኖቹ) ሃገረ ትግራይ አዲስ ሃሳብ አላቀረቡም፤ ሃሳቡን የኮረጁት በብሔራዊነት ጉድለት ከሚከሱት ከሕወሐት ነው” ይለናል፡፡ (ገፅ 261)እናምነገሮችን ከሃገራችን ባሕል አንፃር እንድናይ ግድ ይለናል፡፡ ትርክታችንን እንድንፈትሽ ይጋብዘናል፡፡

የፖለቲካ ባሕላችንን ያስቃኘናል፡፡የትግራይን ባሕልም እንዲሁ፡፡ እናም ከሃገረ ትግራይ ጥያቄ ጋር የተያያዙ የሕግ እና የሞራል ጽንሰ ሃሳቦችን እያነሳ ይሞግታል፡፡በሌላአነጋገር ደራሲው፤ የመገንጠል መብትን ከሞራል አንፃር ይፈትሻል፤ ከሕገ መንግሥት አንፃር ይቃኛል፤ ከዓለም አቀፍ ሕግ አንፃር ያስተነትናል፡፡

በእነዚህና በእነዚህ መሰል ማንፀሪያዎች መገንጠል በየትኛውም ዓይነትና ሁኔታ ተመራጭ እንዳልሆነ ያሰምርበታል፡፡ “….ትግራይኢትዮጵያ ውስጥ ቆይታ አሁን ኢትዮጵያ እየታየባት ያለውን ውስንነት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ለመፍታት መጣር የትግራይምሆነ የኢትዮጵያ ደህንነትና መረጋጋት በተሻለ ደረጃ የማረጋገጥ አቅም ይኖረዋል፡፡

ይህ ሳይሆን ቀርቶ ሃገረ ትግራይ ትመስረት ቢባልሌላው ቀርቶ የማይቀረው ጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ እንኳ የደህንነትና የመረጋጋት ምንጭ አይኾንላትም” (ገፅ

፭

ከመጽሐፉ ጀርባ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ዶ/ር ዮናስ አሽኔ እንዲህ ይላሉ፡-

“የኢትዮጵያታሪክ ረዥም አከራካሪም ነው፡፡ ፖለቲካ ይኼንን አከራካሪ ታሪክ በግብአትነት ይጠቀማል፤ ይህ ያልተገራ ፖለቲካ የተገዳዳሪዎች ትግልየሞላበት ነው፡፡ የሀገርና የሕዝቦችን ነገረ ሕላዌ ያውካል፡፡ ፖለቲካ ማንኛውንም ጉዳይ መገዳደሪያ ከማድረግ አይቆጠብም፡፡

ይህ ፖለቲካ ከታሪክ እየመረጠ በማስታወስ ራሱን ይገልጣል፡፡ ሙሉጌታ አረጋዊ፣ ሃገረ ትግራይ ብሎ በሰየመው መጽሐፉ ፖለቲካው ወደ አደባባይይዞ የመጣውን ሰሞነኛ የመገንጠልና የባይተዋርነት ፖለቲካ ይተነትናል፡፡

”ሌላው አስተያየት ሰጪ ኢኮኖሚስቱ ያዕቆብ በቀለ ደግሞ “መጽሐፉ በታሪክ ድርሳናትና በሕግ መርሆዎች መካካከል የሚደረግ ረቂቅ ሙግት ሲሆንየኢትጵያን የጥንት ሥልጣኔና የዛሬውን የፖለቲካ ምስቅልቅል በአዲስ መነፅር ይመረምራል” ይላል፡፡እኔምበሁለቱ ምሁራን አስተያየት እስማማለሁ፡፡ ለዚህ ነው እኔም የዚህን አጭር ዳሰሳ ርዕስ “ሃገረ ትግራይ – በዘመናት መነፅር ሲታይ”ለማለት የተገደድኩት፡፡

መውጫ

ያምሆነ ይህ ሙሉጌታ አረጋዊ በዚህ ሰሞን ከወደ ሰሜን ፖለቲከኞች የሚሰማውን “ጉም ጉም” አደባባይ አውጥቶ አስጥቶታተል፡፡ በበርካታ መረጃዎችና ማስረጃ እየፈተሸ የጥያቄውን ባዶነት ፍንትው አድርጎ ያሳየናል፡፡ እርግጥ ነው አንዳንድ ሰዎች ርዕስ ተጋፊ ነው ብለውኛል፡፡

አንድን ክልል እንደ ሃገር እውቅና መስጠት ያህል ነው ሲሉም ቅሬታቸውን ነግረውኛል፡፡ነገርግን እዚያው የውጭው ሽፋን ላይ የኢትዮጵያ ሙሉ ካርታ ይታያል፤ በካርታው ላይ የሁሉም ክልሎች
ባንዲራም ቆሟል፡፡ ከዚህ አንፃር፣ለዚህ ፅሁፍ ቅሬታው ሚዛን አልደፋልኝም፡፡

ቢሆንም ደራሲው ቀጣዩ ሕትመት ላይ የርዕሱን ጉዳይ ቢያስብበት ጥሩ ይመስለኛል፡፡በተረፈ“ሃገረ ትግራይ” ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡ በበርካታ የታሪክ መረጃዎች የታጨቀ፣ በርካታ መጽሐፍትን በማጣቀሻነት የተጠቀመ፤ የደራሲውደግነት የታየበት፣ ሊነበብ የሚገባው መጽሐፍ ነው፡፡

ሻሎም!!

ግዮን መጽሔት ቅጽ 8 ቁጥር 232 ሚያዝያ 2018 ዓ.ም

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...

ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ  በአመት ከ1.1 ቢሊዮን ዶላር በላይ ታጣለች

85 በመቶ የሚሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በግብርናው ዘርፍ የተሰማራ ሲሆን...