15 ኢትዮጵያውያን ሰኞ ምሽት ወንዙን ተሻግረው ወደ ቦትስዋና ለመግባት ሲጠቀሙበት የነበረው ታንኳ መገልበጡን፤ የዛምቢያ ፖሊስ አገልግሎት እና የኢሚግሬሽን መምሪያ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ከአደጋው የተረፉ ሁለት ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን ሦስቱ ግለሰቦች የት እንዳሉ እስካሁን አለመታወቁን የዛምቢያ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
የዛምቢያ ባለሥልጣናትየሰለባዎቹ ፍለጋ፣ የተረፉትን ተከታትሎ የማግኘት እና ከአደጋው ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን የማጣራት ሥራ መቀጠሉን ገልጸዋል።
መረጃው እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት አስከሬን ባለመገኘቱ የኢትዮጵያውያኑ መስጠም የፍለጋ ውጤቱ እስኪታወቅ በይፋ እንዳልተረጋገጠ የጋራ መግለጫው አክሎ ገልጿል።
