አዳነች አቤቤና የዓለም ባንክ በትራንስፖርት ዘርፍ አዲስ ስምምነት አደረጉ

Date:

⚡️

የአዲስ አበባ ከተማን የትራንስፖርት አገልግሎት ለማዘመን ከዓለም ባንክ ጋር ፍሬያማ ውይይት መደረጉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።

ከንቲባዋ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ከሆኑት ማርያም ሳሊም ጋር በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

የውይይቱ ዋና ዓላማ የከተማዋን ትራንስፖርት ማሻሻልና በተለይም “E-mobility” (የጭስ አልባ ትራንስፖርት) ተደራሽነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማስፋፋት ነው።

ይህ አጋርነት በዘርፉ የተሰማሩ የግል ድርጅቶችን ለመደገፍና የተጀመረውን የልማት ስራ ለማጠናከር ትልቅ እገዛ እንዳለው ከንቲባዋ ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለማርያም ሳሊም እና ለቴክኒካል ቡድናቸው በራሳቸውና በከተማው ህዝብ ስም ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...