ዕንባ ጠባቂ ከቀረቡለት አቤቱታዎች 84% በመንግስታዊ ተቋማት ላይ የቀረቡ ናቸው

Date:

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም በተጠናቀቀው የ2018 በጅት ዓመት ከቀረቡለት አቤቱታዎች መካከል 84 በመቶዎቹ በመንግስት ተቋማት ላይ የቀረቡ እንደሆኑ አስታውቋል።

የተቋሙ ዋና ዕንባ ጠባቂ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 1ሺህ 867 አቤቱታዎች በ45 ሺህ 189 ሰዎች ቀርበዋል።

ከእነዚህ አቤቱታዎች መካከል 1ሺህ 571 ወይም 84.5 በመቶ የሚሆኑት በመንግስት ተቋማት ላይ የተመሩ ሲሆን፤ ቀሪዎቹ 296 አቤቱታዎች በግል ድርጅቶች ላይ የቀረቡ መሆናቸው ተገልጿል።

አቤቱታዎቹ በስራ፣ በጡረታ፣ በይዞታ እና በካሳ ጥያቄዎች ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ምሆናቸውንም የተቋሙ ዋና እምባ ጠባቂ አስረድተዋል።

ተቋሙ አቤቱታዎችን መሰረት በማድረግ ምርመራዎች የሚያካሂደው ተቋሙ፤ እስከ አሁን ከ2017 በጀት ዓመት የዞሩ 282 መዝገቦችን ጨምሮ በ1ሺህ 104 መዝገቦች ላይ ምርመራ አከናውኗል።

በዚህም 72 አቤቱታዎች መፍትሄ ማግኘታቸውን፣ በደል መፈጸሙ ተረጋግጦ በድርድር 178 መዝገቦች መፍትሄ ማግኘታቸውን እንዲሁም ለ184 መዝገቦች የመፍትሔ ሃሳብ መሰጠቱን ወይዘሮ ስመኝ ተናግረዋል።

ተቋሙ ልዩ ትኩረት የሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎችን እና የአስተዳደር በደልን መከላከልን በተመለከተ ቁጥጥር እያደረገ ሲሆን፤ በሂደቱም ለሚመለከታቸው አካላት ምክረ-ሃሳብ መስጠቱን ዋና ዕንባ ጠባቂዋ ገልጸዋል።

በተጨማሪም፤ በቀጣይ አስተዳደራዊ በደልን አስመልክቶ በተካሄደ ጥናት ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...