የፈረንሳይ ፓርላማ ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ከጥር 2027 ጀምሮ ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ የሚከለክል ሕግ ያጸደቀ ሲሆን፤ ይህም ታዳጊዎች በእነዚህ መድረኮች እንዳይጠቀሙ የከለከለች የመጀመሪያዋ የአውሮፓ ሀገር ያደርጋታል።
ሕጉ በፈረንሳይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ማህበራዊ ሚዲያን ለመጠቀም ዕድሜውን ማረጋገጥ እንዳለበት የሚደነግግ ሲሆን፤ ይህም ውሳኔ የተላለፈው ብሪታንያ እና የአውሮፓ ህብረት ለህጻናት አእምሯዊ ጤንነት ካላቸው ስጋት አንጻር የራሳቸውን ገደቦች በማዘጋጀት ላይ ባሉበት ወቅት ነው።
የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ይህንን እርምጃ በደስታ ተቀብለውታል።
አንዳንዶች የሕጉን ተግባራዊነት ቢጠራጠሩም፣ መንግሥት ግን ዕድሜን ለማረጋገጥ የሚረዱ መሳሪያዎች ውጤታማ እና አስተማማኝ መሆናቸውን አረጋግጧል።
ከግራ ክንፍ የፖለቲካ ወገኖች ትችት ቢሰነዘርበትም፣ የፈረንሳይ ሴኔት እና ብሔራዊ ምክር ቤት እገዳውን ማክሰኞ ዕለት አጽድቀውታል።
ህጉ በሁለት ደረጃዎች ተግባራዊ ይሆናል፡-
ከመስከረም ጀምሮ፡ ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ሰዎች አዲስ መለያ (አካውንት) መክፈት አይችሉም፤ እንዲሁም በማንኛውም አዲስ መለያ ላይ የዕድሜ ማረጋገጫ ያስፈልጋል።
በጥር 2027፡ ይህ ሕግ በነባር መለያዎች ላይም ተተግበሮ ይውላል—ይህም ማለት በፈረንሳይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ማህበራዊ ሚዲያ ለመጠቀም ዕድሜው ከ15 ዓመት በላይ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርበታል።
የሮይተርስ ዜና ወኪል እንደዘገበው ከሆነ፣ እገዳው አንዴ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች በፈረንሳይ የነጻነት እና የመረጃ ተቆጣጣሪ ተቋም የተፈቀዱ የዕድሜ ማረጋገጫ መሳሪያዎችን መጠቀም ይኖርባቸዋል።
ሐምሌ 15/2018 ዓ.ም
ፈረንሳይ ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ ከለከለች
Date:
