በድሬዳዋ ከተማ ጉዳይ ላይ በሀገራዊ ምክክሩ ከምን ስምምነት ላይ ተደረሰ?

Date:

በሀገራዊው ምክክር ላይ የድሬዳዋ ከተማ በፌዴራል ከተሞች ጉዳይ ስር ምክክር ከተደረገባቸው ሁለት ከተሞች አንዱ ነው። ከኦሮሚያ እና ከሶማሌ ክልሎች በተወከሉ የምክክሩ አባላት መካከል ከፍተኛ የይገባኛል ክርክር እንደተደረገባት በምክክሩ ላይ የተሳተፉ ታማኝ ምንጭ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ ሰፊ መነጋገሪያ መሆኑ፣ የድሬዳዋ ጉዳይ ብዙም ትኩረት እንዳያገኝ አድርጎታል።

እስካሁን ያለው የከተማዋ አስተዳደር ምን ይመስላል?

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በሥራ ላይ ባለው የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት አይታወቅም።

ከተማዋ የሶማሌ እና የኦሮሚያ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱባት በመሆኑ፣ በሕግ መሠረት የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ በሚል ከ1985 ዓ.ም. ጀምሮ ለፌደራል መንግሥት ተጠሪ ሆና ስትተዳደር ቆይታለች።

የከተማዋን አስተዳደር እና ለፌዴራል መንግሥት ተጠሪ ሆና መዋቀሯን የሚደነግገው ሕጋዊ ሰነድ፣ ማለትም “የድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ” አዋጅ ቁጥር 416/1996 የተዘጋጀው ደግሞ በ1996 ዓ.ም. ነው።

ቻርተሩ የተዘጋጀው ዘላቂ የሆነ ሕጋዊ መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ የድሬዳዋ ከተማ ለጊዜው እራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበት ሕጋዊ መሠረት እንዲኖረው ለማስቻል ስለመሆኑ በአዋጁ መግቢያ ላይ ተጠቅሷል።

ይህ ቻርተር በተዘጋጀ ማግስት በቀጣዩ ዓመት ከተካሔደው የ1997 ዓ.ም. ምርጫ በኋላ የከተማዋ አስተዳደር የተለየ ቅርጽ ይዞ ቀጥሏል።

ይኸውም 40-40-20 የሥልጣን ክፍፍል ያካተተ ሲሆን እስከ አሁንም ድረስ በሥራ ላይ ያለ ነው

በቻርተሩ ውስጥ በግልፅ ባልተጠቀሰው በዚህ የሥልጣን ክፍፍል መሠረት፣ የኦሮሞ እና የሶማሌ ተወላጆች 40፣ 40 በመቶውን የከተማ አስተዳደር ምክር ቤት እና የካቢኔ ቦታ ሲከፋፈሉ፣ የተቀረው 20 በመቶ በከተማዋ ለሚኖሩ ሌሎች ብሔረሰቦች እንዲሆን ተደርጓል።

የከንቲባነቱን ቦታ ደግሞ የሁለቱ ብሔሮች ተወላጆች ተራ በተራ እየተፈራረቁ ይይዛሉ። ይህ “በፖለቲካዊ ውሳኔ” የተተገበረው እና ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ የዘለቀው የሥልጣን ክፍፍል በብዙዎች ዘንድ ትችት ሲሰነዘርበት ቆይቷል።

በአስተዳደሩ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎች

ይህን አካሔድ የሚተቹ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎችም ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም። ከምሁራን በተጨማሪ አስተያየታቸውን የሰጡን ሦስት የከተማዋ ነዋሪዎችም የነበረውን የከተማዋ አስተዳደር አወቃቀርን የሚተቹ ናቸው።

በሥልጣን ክፍፍሉ ደስተኛ አለመሆናቸውን ማንነታቸው እንዲታወቅ ያልፈለጉት አስተያየት ሰጪዎቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይህ አካሔድ “የከተማዋ እድገት ወደ ኋላ እንዲቀር እና የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲኖር ከፍተኛ ሚና አለው” ይላሉ አንዱ ምክንያታቸውን ሲያስረዱ።

የሥልጣን ክፍፍሉ “የከተማዋን ነዋሪዎች እና ተወላጆች ያገለለ ነው” ሲሉም ይተቻሉ። ነገር ግን “ዋናው የምንፈልገው ሰላማችንን ነው” በማለት ይህ ሁኔታ ብዙም እንደማያሳስባቸው አንስተዋል።

ካነጋገርናቸው ውስጥ ነዋሪዎች መካከል ሌላኛው ግለሰብ ለ40 ዓመታት ያህል በድሬዳዋ የኖሩ ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በከተማዋ እየተስተዋለ ላለው አለመረጋጋት ያለውን የአስተዳደሩን አወቃቀር ተጠያቂ ያደርጋሉ።

የሰላም እና የፍቅር ተምሳሌት ተደርጋ የምትወሰደው “የበረሃዋ ገነት” ድሬዳዋ፣ ከ2008 ዓ.ም. ወዲህ “አዲስ ሆናብኛለች” ይላሉ። በ2008 ዓ.ም ተከስቶ የነበረው እና ለተወሰነ ጊዜ አልፎ አልፎ የተስተዋለው “የብሔር እና የሃይማኖት ይዘት” እንዳለው የገለፁት ግጭት በ40 ዓመታት የከተማዋ ቆይታቸው የማያውቁት መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ድሬዳዋ የተረጋጋች እና ሰላማዊ ከተማ እንደሆነች የሚገልፁት ግለሰቡ “እሱ ሳይናጋ እንዲቀጥል ነው ፍላጎቴ” ብለዋል። ነገር ግን “በማንኛውም ጊዜ ግጭት ሊፈጠር ይችላል” የሚል ስጋት እንዳላቸውም አልሸሸጉም።

ፎቶ በስልኳ የምትነሳ የድሬዳዋ ነዋሪ

በድሬዳዋ ጉዳይ ላይ ምን ስምምነት ተደረሰ?

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...

«ግብጽ ዛቻውን አቁማ ወደ ድርድር ትግባ!»

ታዋቂው የአፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝ ዶ/ር ዴቪድ ማትሳንጋ ግብጽ በኢትዮጵያ...