የኢትዮጵያ ደረጃዎች ቦርድ አዲስ ምልክት አጸደቀ

Date:

የኢትዮጵያ ደረጃዎች ቦርድ መጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡ ምርቶች የሚሆን አዲስ የደረጃ ምልክት አጽድቋል።

ይህ ምልክት ከዉጪ የሚገቡና የኢትዮጵያ ደረጃ የወጣላቸውን ምርቶች ከሀገር ውስጥ ምርቶች ለመለየት ያስችላል ተብሏል።

በገበያ ላይ ፍትሃዊ የሆነ ውድድር እንዲኖር እንደሚያደርግ እና ሸማቾች የውጭ ምርቶች ጥራታቸውን ጠብቀው መምጣታቸውን እንዲያውቁ እንደሚረዳ ተገልጿል።

ካፒታል ያገኘዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ይህ አዲስ የደረጃ ምልክት የኢትዮጵያ ደረጃ ለወጣላቸው ከውጭ ለሚገቡ ምርቶች ብቻ የሚውል ይሆናል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...