ይህ ሕንጻ የተቋሙን አርቆ አሳቢነት የሚያሳይ ነው”

Date:

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያስገነባቸው ግዙፍ ዘመናዊና ሁለገብ ዓለም አቀፍ የጉባኤ ማእከል በተመረቀበት ደማቅ መርሐ ግብር ላይ ባስተላለፉት ቃለ ቡራኬና በረከት፡- ሕንጻው የቅዱስ ሲኖዶስ፥ የስብከተ ወንጌልና ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤያትን ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለማካሄድ የሚያስችሉ አዳራሾች የተካተቱበት፣ ዋጋው በተሠራበት ቁሳቁስ ብቻ ሳይሆን በተገነባበት ዓላማ ጭምር የሚለካና ልዩ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡

ቅዱስነታቸው አያይዘውም ሕንጻው የቦታ አጠቃቀምንና ማራኪ ሥነ ሕንጻን በማዋሐድ ተገንብቶ መጠናቀቁን ጠቅሰው፣ የቤተ ክርስቲያናችን ሐዋርያዊ አገልግሎት በሚፈለገው ልክ የሚጠናከርበትና ለቀጣዩ ትውልድም የምናቆየው ዘመን ተሻጋሪ ሀብት በመሆኑ ከፍ ያለ መንፈሳዊ ደስታ ይሰማናል ብለዋል።

የአዲሱ ሕንጻ የግንባታ ሐሳብ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፭ኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ መዋዕለ ሕይወት ተነሥቶ፤ ዕቅዱን የማደራጀትና የግንባታ ተግባሩ በየዘመነ ሢመታቸው ቤተ ክርስቲያንን የመሩ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በኃላፊነትና በትጋት አሻራቸውን እያሳረፉበት እንዲሁም ብዙዎች በዕውቀታቸው፥ በጉልበታቸው እየተሳተፉበት ለዚህ በዘመን ደርሶ በልዩ ጥራት መጠናቀቁን ያበሰሩት ቅዱስነታቸው፤ በሥራ ላይ ለሚገኙት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፥ በየደረጃው ለሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ የሥራ ሓላፊዎች እንዲሁም ለሁሉም የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በመጨረሻም፤- በአዲሱ ጽርሐ ተዋሕዶ የሚደረጉ ጉባኤያት ሃይማኖትን ለማጽናት፥ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት፥ ለሕዝቡ ደኅንነትና ለሀገር ሰላም አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ፥ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ከነሙሉ ክብሩ ለትውልድ የሚሸጋገርባቸው ሊሆኑ እንደሚገባ ከአባታዊ አደራ ጋር አሳስበዋል።

በክብር እንግድነት የተገኙት ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ የጽርሐ ተዋሕዶ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከልና ሁለገብ ሕንጻ በተመረቀበት ወቅት በመልእክታቸው እንደ ገለጹት የሃይማኖት ተቋማት ታሪክንና ቅርስን በመጠበቅ፣ሥነ ጽሑፍን በማቆየት፣ሀገራችን ከዓለም ጋር ያላትን ግንኙነት ጠብቆ በማቆየት፣ባልጠበቅናቸው ሀገሮች ሁሉ በመገኘት የእምነቱን ብቻ ሳይሆን የሀገራችንን ገናናነትና ታሪካዊነት በማስረጽ ያለቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምን ያህል ጉልበትና ተቀባይነት እንዳላት የሚያውቅ ያውቃል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክን በመዘገብ ቅርሶቻችንን ከጥፋት በመጠበቅ፣ ብራና ዳምጣ፣ ቀለም በጥብጣ፣ፊደል ቀርጻ ብዙዎችን ለወግ አብቅታለች።

ልጆቿም የዜማና የስዕል ጥበብን ለዓለም አስተዋውቀዋል።
በገላጣ ሜዳና ተራሮች ላይ ደኖችን ካየን ይህ በረከት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ እና የቻይና አየር መንገዶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በቻይና...

ሁቲዎች በሳዑዲ የነዳጅ ኩባንያ አስተዳደር ሕንጻ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በእሳት ተያያዘ

የሳዑዲ አረቢያ የኢነርጂ ሚኒስቴር በአገሪቱ ምሥራቃዊ ግዛት የሚገኘው ከዓለም...

የሹመት ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ሹመት የሰጧቸው አመራሮች፡- 1. አቶ...

እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን …

በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ...