የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

Date:

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ2019 ዓ.ም የጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ የመክፈቻ መግለጫ የሰጡት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ለመቀበልም ሆነ ለመስጠት መታመን መሠረታዊ እንደሆነና ጉባኤው በቤተ ክርስቲያን መታመን እንዲኖር የመሥራት መለኮታዊ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

የሀብት አጠቃቀም፣ የምዕመናን አያያዝ እና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ዘመኑን የሚመጥን እንዲሆን ክፍተቶችን በመፈተሽ ዘላቂ መፍትሔ ማስቀመጥ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተልዕኮውን ማከናወን የሚችለው አገር ሰላም ሲሆን በመሆኑ፣ ችግሮችን ለመፍታት ከጸሎት ባለፈ የማግባባትና የማስታረቅ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በጉባኤው ለሀገር ሰላም የሚኖረውን ሚና በተመለከተ ውይይት እንደሚደረግና ለባለድርሻ አካላት የሰላም ጥሪ እንደሚ አስተላለፍ ተጠቅሷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አይበገሬው ፍቃዱ —-  ( ከጋዜጠኛ ሁሴን ከድር )

ትናንት ( ቅዳሜ ጥቅምት 14 2019 ዓ.ም ) የቀድሞ...

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ10 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ጥቅምት 12 ቀን 2019...

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ የፕላቲንየም ብራንድ የማስተር ካርድ ይፋ አደረጉ

ዳሸን ባንክ እና ሼባ ማይልስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ደንበኞች የፕሪሚየም...

የአሜሪካ የደህንነት ኃላፊ ኢራንን አስጠነቀቁ

ቡሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ጄይ ክላይተን አርብ ዕለት ኢራን በውጭ...